"የሐዋርያት ሥራ" ክፍል ሁለት
https://youtu.be/1EEj-7FcQsI
https://youtu.be/1EEj-7FcQsI
YouTube
ገድል እና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ | የሐዋርያት ሥራ ጥናት | ክፍል 2 - በዲያቆን አቤል ካሳሁን
#like #subscribe #share
በዚህ ቪድዮ የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል የሆነውን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በኦርቶዶክሳዊ እይታ እና ከአባቶቻችን ባገኘነው ትውፊት ከዲያቆን አቤል ካሳሁን ጋር እናጠናለን። ቪድዮውን ለወዳጅዎ በማጋራት የቤተ-ክርስቲያችንን ትምህርት ተደራሽነቱን ያስፋፉ።
እግዚአብሔር ያክብርልን!!
©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media -2013|2021

Dn Abel Kassahun Mekuria pinned «"የሐዋርያት ሥራ" ክፍል ሁለት https://youtu.be/1EEj-7FcQsI»
ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ቃል "አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ?" የሚል ነበር። ልባቸው በኀዘን ለተሰበረ እና ዓይኖቻቸው በእንባ ለተሞላ ሁሉ ጌታ ቅርብ ነው። "ለምን ታለቅሳላችሁ?" ብሎ ይጠይቃል። በሰው ኀዘን ያዝናል፣ ልጇን ከሞት እንዳስነሣላት መበለትም "አታልቅሱ" ብሎ ያጽናናል። በመከራ ጊዜ "አምላኬ፣ አምላኬ" ተብሎ በእውነት ሲጠራ ይሰማል። ሁሉን የሚችል አምላክ፣ እርሱ ለኀዘንተኞች መጠጊያ ይሆናል።
ያዘነና የተከዘውን ሰው ቸል የሚል፣ ለሰው ድካም የማይራራ አምላክ የለንም። እንዲህ ስላለውም አምላክ አባቶቻችን አልነገሩንም፣ እኛም አልሰማንም።
"ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ"
መዝ 86፥7

ታዋቂው የመድረክ ቴያትሮችና የረጃጅም ልቦለዶች ደራሲ ጀርመናዊው ኸርነስት ቶለር፣ በሥራዎቹ ውስጥ የጸረ ናዚ አቋም ያራምድ ነበር። በዚህም ምክንያት በጊዜው የነበሩ ፋሺስት ባለ ሥልጣናት ኸርነስት ከጻፋቸው መጻሕፍት ውስጥ አንዱን ያለ ምንም ማወራረጃ በቁሙ ቅርጥፍጥፍ አድርጎ እንዲበላ እንዳደረጉት ይነገራል። ያሳዝናል!
ደግሞ የመጽሐፋን ፍሬ ሐሳብ በውስጣቸው ለማስቀረት ያለ አስገዳጅ "መጽሐፍ በል" የሆኑም እንደ ኦዴር ያሉ ደራሲዎች ነበሩ። ይገርማል!
ከአገራችንም ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ታመው በነበሩ ጊዜ ለመድኃኒት እንዲሆናቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ገጻት አንዳንዱን ይበሉ እንደ ነበር የጻፉ አሉ። አይይይ እምነት!
በእርግጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይም ነቢየ እግዚአብሔር ሕዝቅኤል "ይህን መጽሐፍ ብላ" የሚል ግብዣ እንደ ቀረበለት ተጽፎ እናነባለን። "ብላ" የሚል ግብዣ ብቻም ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር "መጽሐፋን አጉርሶታል"።(ሕዝ 3፥1-2) ሕዝቅኤልም ጉርሻው እንደ ማር የጣፈጠው መሆኑን አልሸሸገንም። ይሁን እንጂ ይህ ነቢዩ የጎረሰው መጽሐፍ እኛ ከምናውቀው ግዙፍ ቁስ የተዘጋጀና ምንም ጣዕም የሌለውን ሳይሆን፣ ከማርና ወተት ይልቅ የሚጥም ረቂቁ የእግዚአብሔርን ቃል ነው።
እኛስ አበው የመጻሕፍትን አድባር ወጥተው፣ የትርጓሜን ቆላ ወርደው ያዘጋጁልንን ይህንን "የሐዋርያት ሥራ ትርጓሜ"ን የቃለ እግዚአብሔር መዓድ ለምን አንበላም? የጎርሻ ያህል ተዘጋጅቶልናል። ይጉረሱ እንጂ?!
https://youtu.be/JuCmW43DVtI

ኢየሱስ የመረጣቸው ሐዋርያት - ዲያቆን አቤል ካሳሁን - የሐዋርያት ሥራ ጥናት +++ክፍል 3+++
#like #subscribe #share
በዚህ ቪድዮ የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል የሆነውን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በኦርቶዶክሳዊ እይታ እና ከአባቶቻችን ባገኘነው ትውፊት ከዲያቆን አቤል ካሳሁን ጋር እናጠናለን። ቪድዮውን ለወዳጅዎ በማጋራት የቤተ-ክርስቲያችንን ትምህርት ተደራሽነቱን ያስፋፉ።
እግዚአብሔር ያክብርልን!!
©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media -2013|2021
በዚህ ቪድዮ የመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ክፍል የሆነውን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በኦርቶዶክሳዊ እይታ እና ከአባቶቻችን ባገኘነው ትውፊት ከዲያቆን አቤል ካሳሁን ጋር እናጠናለን። ቪድዮውን ለወዳጅዎ በማጋራት የቤተ-ክርስቲያችንን ትምህርት ተደራሽነቱን ያስፋፉ።
እግዚአብሔር ያክብርልን!!
©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media -2013|2021
👍1
"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ፣ ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋራ ወደኔ ነይ፡፡ ካንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽን ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊልኝ ዘንድ፡፡ ድንግል ሆይ፣ የቃልን ካንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአስተማሩ፣ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ሐዋርያት ጋራ ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ፣ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕታት፣ እርሳቸው ሁለት ልሳን ያለው ሰይፍ የሚታጠቁ ድል የሚነሱ የንጉሥ ሠራዊት ናቸው፡፡ ከርሳቸው ማኅበር ጋራ ደግሞ በረድኤት ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ በማመንዘር እድፍ ልብሳቸውን ካላሳደፉ፣ ለመንፈስም ማደሪያ ከሆኑ ንጹሓን ደናግል ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
አርጋኖን ዘአርብ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
አርጋኖን ዘአርብ
+++ "ፍቅርና ፍርሐት"+++
በሰው መካከል ያለ ቀረቤታ ሲጠነክርና ፍቅሩ ያደገ ሲመስል መከባበርና ሐፍረት እቀነሰ ሊመጣ ይችላል። "አሁንማ መፈራራት አያስፈልግም"፣ "እንደ ስሜትህ መሆን ትችላለህ?" የሚሉ ቃላቶችን በጊዜው ለጠበቀው ወዳጅነታቸው መመሪያ ጥቅስ ሊያደርጉትም ይችላሉ። ነገር ግን ጉዳዩ ለከቱን ያለፈ ቀን ይዞባቸው የሚመጣው የጠብ ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚመለስ አይደለም። ሁል ጊዜ በጸና ፍቅር ውስጥም ቢሆን መኖር ያለበት "ንጹሕ ፍርሐት እና ሐፍረት" አለ። እርሱ ደግሞ መከባበርን ያመጣል።
የእግዚአብሔርን ፍቅር በሚገባ ላልቀመሰ ሰው ከገጸ ምሕረቱ ይልቅ ገጸ መዓቱ ይጎላበታል። ስለዚህ ትእዛዛቱን ለመፈጸም የመጀመሪያ ምክንያት የሚሆነው "በሥጋዬ እንዳይቀስፈኝ፣ በነፍሴ እንዳያጠፋኝ" የሚለው ፍራቻው ነው። እንዲህ ያለውን ፍርሃት መጽሐፈ መነኰሳት "ፍርሃተ አግብርት"/"የባሮች ፍርሐት" ብሎ ይጠራዋል። ይህም እንደ እኛ ባሉ ጀማሪ ክርስቲያኖች ኅሊና ውስጥ የሚሯሯጥ ፍርሃት ነው። ፍቅሩን ለሚያስብ የበረታ ክርስቲያን ግን ባላደርግ እቀጣለሁ ብሎ ሳይሆን፣ ፈጣሪውን ስለሚወድ ብቻ ትእዛዙን ይፈጽማል።(ዮሐ 14)
ይሁን እንጂ ከፍቅር ላይ የደረሱም ቅዱሳን ቢሆኑ እግዚአብሔርን መፍራታቸው የማይቀር ነገር ነው። ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር መልሰው እርሱን እንዲዳፈሩት ምክንያት አይሆናቸውም። የቅዱሳኑ ፍርሃት ግን "ምን ያደርገኝ ይሆን" የሚል የባርያ ፍርሃት ሳይሆን፣ "እንዳያዝንብኝ፣ እንዳይከፋብኝ" ከሚለው ልጃዊ ፍቅር የመነጨ ነው።
በተጨማሪም የመለኰቱ ርቀት፣ የባሕርዪው ምልዓት በልብ ታስቦ የማይደረስበት መሆኑን ዐውቀው፣ በልባቸው ጉልበት እየራዱ አይመረመሬነቱን በአንክሮ ማድነቃቸው ነው "እግዚአብሔርን መፍራታቸው"።
ሐዋርያው "ፍጹም ፍቅር ፍርሐትን አውጥቶ ይጥላል" ይለናል።(1ኛ ዮሐ 4፥18) ምን ማለት ነው? ስለ የትኛው ፍርሃት እየተናገረ ይሆን? ቅዱስ ዮሐንስ የሚናገረው አንደኛ "ፍርሐተ አግብርት" ስለተባለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ እሳት ስለቱን እንዲሁም በሥጋ የሚመጣውን ስቃይ ተሰቅቆ እርሱን ከመካድ ስለሚያደርሰው "ጎጂ ፍርሐት" ነው።
በቀረው ግን ፍጹም ፍቅር ሥጋዊ ፍርሐትን እንጂ፣ እግዚአብሔርን መፍራትን ከውስጣችን አውጥቶ አይጥልም!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com

+++ "አብረን ዝም እንበል" +++
አባ በምዋ (Abba Bemwa) ዓለምን ትቶ ወደ በረሃ በሄደ ጊዜ፣ ለዚህ አዲስ ሕይወቱ የሚጠቅመውን ምክር ይሰጡት ዘንድ ወደ አንድ ቅዱስ አረጋዊ ቀርቦ "ምን ላድርግ" ሲል ጠየቃቸው። እኒህም አረጋዊ ንግግራቸውን የጀመሩት "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ" በሚለው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር ቃል ነበር። (መዝ 39፥1) አባ በምዋም ይህንን የመጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ "ይበቃል አባቴ፣ ይህን ተምሬ እስክፈጽም ድረስ ሌላ ምንም አዲስ ትምህርት አይንገሩኝ" በማለት ወደ በዓቱ ሄደ።
ከዚያም ቀን ጀምሮ ለብዙ ጊዜያት ወደ አረጋዊው አልተመለሰም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋዊው ጻድቅ አባ በምዋን አግኝተው ለምን ለሌላ ተጨማሪ ትምህርት መልሶ ወደ እርሳቸው እንዳልመጣ ጠየቁት። እርሱም "እመኑኝ አባቴ፣ ገና የመጀመሪያውን ትምህርት በሚገባ አልተማርኹትም" ሲል መለሰላቸው። ከረጅም ዓመታትም በኋላ ወዳጁ የሆነ አንድ መነኩሴ የሰማውን የነቢዩ የዳዊትን ቃል እስከ አሁን አጥንቶ ጨርሶ እንደሆነ አባ በምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም "በዚህ የነቢዩ ቃል ላይ ለማሰላሰል እና በሚገባ ወደ ተግባር ለመቀየር አርባ አምስት ዓመታት ወስዶብኛል" ሲል በትሕትና መለሰለት። የአባ በምዋን ታሪክ የጻፈልን ቅዱስ ጰላድዮስ እንደሚናገረው አባ በምዋ በሕይወቱ ሁሉ ፍጽምት የሆነች የዝምታን ሕይወት የመራ ሲሆን፣ በሞቱም ጊዜ "ምነው ይህን ባልተናገርኩ" የሚል አንድም የሕሊና ወቀሳ ሳያገኘው በሰላም አርፏል።
ቅዱስ እንጦንስም በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል መክሯቸው ነበር ፦ "ዝም በሉ፤ ዝምተኛን ሰው እግዚአብሔር በፊቱ ካሉት ሠራዊተ መላእክት እንደ አንዱ ይቆጠረዋልና"
ስለዚህ ከመላእክት ጋር እንቆጠር ዘንድ አብረን ዝም እንበል!

+++ የጽሙና ጊዜ አለህ? +++
የቆርቆሮና የብረት ጩኸት ጋጋታ ባለበት ውብና ለስላሳ የሆነውን የዋሽንት ድምጽ መስማት የሚቻለው ማን ነው? ሁከትና ረብሻ በሚነግስበት፣ የማይቋረጥ ግፊያና አለመረጋጋት ባለበት የሰዎች ግርግር ውስጥ ሆነህ እንዴት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ልትሰማ ትችላለህ? የእግዚአብሔርን ድምጽ በአውሎ ነፋስ ፋጨት፣ በምድር መናወጥ፣ በሚያስገመግም የእሳት ድምጽ ውስጥ አታገኘውም። እርሱ የሚናገረው ከእነዚህ ሁሉ በኋላ በሚሆነው "ትንሽ የዝምታ" ጊዜ ነው።(1ኛ ነገ 19፥12)
ልክ የመድኃታችንን የልብሱን ጫፍ በስውር ነክታ ከቁስሏ እንደ ተፈወሰችው ሴት፣ አንተም የነፍስህን ቁስል ለማድረቅ በመቅደሱ የሞላውን የጌታን የልብሱን ዘርፍ በምሥጢር የምትዳስስበት የብቻ ጊዜ ያስፈልግሃል?
ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ ከሰው ርቀህ በርረህ ወደ ፈጣሪ የምትሄድበት የጽሙና ጊዜ ይኑርህ።
ጌታን ያጠመቀውና ለብዙዎች በብርሃኑ ደስ የሚያሰኝ "የሚነድ መብራት" የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሁሉ በፊት ብቻውን ከአምላኩ ጋር በበረሃ ነበር። የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እነዚያን ሁሉ ሰማያዊ ምሥጢራት የተመለከተው ብቻውን በፍጥሞ ደሴት ሆኖ ነው። ስሙን በአሕዛብ፣ በነገሥታቱና በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ይሸከም ዘንድ የተመረጠው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ከሁሉ አስቀድሞ ግን የመረጠው አምላኩ መንፈሳዊውን ኃይል ያስታጥቀው ዘንድ የገዛ ድክመቶቹን ተሸክሞ ብቻውን ወደ አረብ በረሃ ገስግሶ ነበር።
ያንተስ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በመንፈስ የምትጎለምስበት በረሃህ ፣ እንደ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን የምትዘከርበት ፍጥሞ ደሴትህ፣ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ በነፍስ ታድሰህ የምትወጣበት አረባዊ ገዳምህ የት ነው? መቼ መቼስ ወደዚያ ትወርዳለህ?
ፎቶው: በንጥርያ የሚገኘው የአል-ባራሞስ ገዳም ነው። በብቸኝነት ሕይወቱ ይታወቅ የነበረው አባ አርሳንዮስ፣ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል በንጥርያ ገዳም ወዳለችው ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ "ሰዎች እርሱን እንዳያዩት፣ እርሱም ሰዎችን እንዳያይ" ተደብቆ(ተከልሎ) የሚያስቀድስባት ምሰሶ ነበረችው። ይህች ምሰሶ አሁንም ድረስ በገዳሙ ትገኛለች።

በዕውቀትና የሥራ ልምድ የተሻለ ከሚባል ሰው ጋር አብሮ መሥራት ያስደስትህ ይሆናል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመ ጥር ከሆነ ባለሙያ ጋር መሥራት ደግሞ ያለውን ስሜት በቃላት ለመግለጽ ሊከብድህ ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቤት የሚያገለግል ሰው ከማን ጋር የሚሠራ ይመስልሃል? ሐዋርያው እንዲህ ሲል ይመልሳል "ከእርሱ(እግዚአብሔር) ጋር አብረን የምንሠራ ነንና"። (1ኛ ቆሮ 3፥9) ለጥበቡ ስፍር ቁጥር ከሌለው፣ ሁሉን ከሚችልና በሁሉ ካለ አምላክ ጋር አብሮ ከመሥራት የሚበልጥ ክብር ከየት ይገኛል?! የዕውቀት ተከፍሎ ካለበት፣ ስሕተት ሊገኝበት ከሚችል ደካማ ሰው ጋር አብሮ መሥራት ይህን ያህል የሚያኮራ ከሆነ፣ ሁሉን ከሚያውቅ ፈጽሞ ከማይሳሳት ኃያል አምላክ ጋር "አብሮ ሠራተኛ መሆን" ምን ያህል እጥፍ ድርብ ያኮራ ይሆን?!
ይህን መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚጋሩበትን የኦሮሚኛ (Afaan Oromoo) ቻናል ይቀላቀሉ። ይማሩ፤ ያስተምሩ፤ ያንብቡ፣ ያስነብቡ፤
Public Channel :- Dn Abeel Kaasahuun - Afaan Oromoo
Description :- Chaanaalii kana Irraatti Dn Abeel Kaasahuniin Barumsi Hafuuraa Darba.
(በዚህ ቻናል ላይ በዲ/ን አቤል ካሰሁን መንፈሳዊ ትምህርቶች ይተላለፋል!)
https://tttttt.me/AbeelK_Afaan_Oromoo

Telegram
Dn Abeel Kaasahun-Afaan Oromoo
Chaanaala kanarratti Karaa Dn Abeel Kaasahuniin Barumsi Hafuuraa Afaan Oromoon Darba
በዜና አበው እንደ ተጻፈ አንድ ቅዱስ አባት ወደ እስክንድርያ በወረደ ጊዜ፣ በዚያ አምላክ የለሽ (Atheist) የሆኑ ጨካኝ ሰዎች አገኙት። እነዚያም ሰዎች ቅዱሱን ከብበው ይሰድቡት፣ ይረግሙትና ይደበድቡት ጀመር። ያም ቅዱስ "ለምን ትመቱኛላችሁ? ለምንስ ትሰድቡኛላችሁ?" የሚል አንድ እንኳን ተቃውሞ ከአንደበቱ አላሰማም። እንዲያውም ፊቱ ላይ ፍቅርና ኃዘኔታ ይነበብ ነበር። በኋላም ከደብዳቢዎቹ አንዱ "አንተ የምታምንበት ያ ናዝራዊ ምን ምን ተአምራት ሠራ? እስኪ ንገረን?" ሲል ጠየቀው። እስከዚያች ጊዜ ድረስ ስድብና ዱላውን በዝምታ ሲቀበል የነበረው አባት አሁን ግን ጸጥታውን ሰብሮ እንዲህ ሲል መለሰ "ከጌታዬ ተአምራት አንዱ በስድባችሁና በድብደባችሁ መካከል እኔን ደስተኛ አድርጎ ማቆሙ ነው"
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
+++ ‹እንሞታለንና…› +++
ለእውነተኛው እና ዘላቂነት ላለው ሕይወት ዳግመኛ የምንወለድበትን የሞታችንን ሰዓት አንርሳ፡፡ ይህችውም የተለየች እና ምሥጢራዊ የሆነች ሰዓት ናት፡፡ እኛ ሰዎች እድሜያችን እየጨመረ በመጣ ቁጥር ወደ ሞት የበለጠ እየቀረብን እንሄዳለን፡፡ የምድራዊ ሕይወታችን ፍጻሜ እየተቃረበ ሲመጣ ዘላለማዊውን ሕይወት ለመጀመር በእጅጉ እንዳረሳለን፡፡
በቀዳሚው ልደታችን ወደዚህች ዓለም ስንመጣ ከማልቀስ በቀር ወዴት እንደምንሄድ ለመጠየቅና ለመምረጥ እድሉ አልነበረንም፡፡ ለአዲስ ሕይወት በምናደርገው ዳግመኛ ልደት (ሞት) ግን በወደድነው ሥፍራ ሄደን እንኖር ዘንድ የመምረጥ ነጻነቱን ፈጣሪ ሰጥቶናል፡፡ የዚህን ምርጫ ጠቃሚነት ያወቅን ስንቶቻችን እንሆን?
ከተወለድንበት ጊዜ አንሥቶ ወደ እርሱ እንደምንጓዝ እያቅን ሞትን ስለምን እንፈራዋለን? ይህን እውነት ለመረዳትና በእርሱም ላይ ያለንን ፍራቻ ለማስወገድ የሚበቃ የጽሙና ጊዜ አጥተን ይሆን?
ክርስቲያኖች ግን በዚህ እድለኞች ናቸው፡፡ በእነርሱ ያለው እምነትና ተስፋ ይህን የሞትን ምሥጢራዊ መጋረጃ ስለሚያስወግድላቸው በእርሱ በኩል የሚተላለፈውን ረቂቅ መልእክት ሳይቸገሩ ማየት ይችላሉ፡፡ ይህ ከመጋረጃው ጀርባ ያለ በሞት በኩል የሚተላለፈው ስውር መልእክት ምንድር ነው?
ቅዱስ ዮንሐስ አፈወርቅ መሪር ኃዘን እንደማይገባ እና ኃዘንተኞች ሊያሳዩት ስለሚያስፈልግ ትእግስት ባስተማረበት ድርሳኑ ላይ ‹‹ወደ ሌላኛው ሕይወት ለመጓዝ በመንገድ ላይ ባሉ ሰዎች ዙሪያ እስኪ እንሰብሰብ፡፡ ተቀመጡ!፤ በፊታችሁም ያለውን አስከሬን አትረብሹ…ራሳችሁን በማረጋጋት ታላቁን ምሥጢር አይታችሁ ተረዱ፡፡……በዚህም ዝምታ ውስጥ ራሳችሁን እንዲህ ስትሉ ጠይቁ…‹እኔን የሚመለከት ይህ ታላቅ ምሥጢር ምንድር ነው? ትላንት እወደው የነበረው ሰው ፤ አሁን ግን በፊቴ አስፈሪ ሆነ፡፡ ትላንት አብሮኝ የነበረው ፤ አሁን ግን እንግዳ ሆኖ ታየኝ፡፡ ከጥቂት ጊዜያቶች በፊት ያቀፈኩት እርሱን ፤ አሁን ግን ለመንካት እንኳን ፈቃደኛ አይደለሁም፡፡ ለእርሱ እንደ ራሴ አድርጌ አለቀስኩለት ፤ በድኑን ግን የእኔ እንዳልሆነ ነገር ፈጥኜ አስወገድኩት (ቀበርኩት)፡፡›› ሲል በማይናገሩት አስከሬኖች አንጻር ያለውን የእኛን የነገ እጣ ፈንታ ያሳያናል፡፡ በርግጥም ዛሬ ሞተው በፊታችን የምናያቸው አስከሬኖች ላይ የሚሆነው ነገር ሁሉ ነገም እኛ ላይ ሊደገም ተራችንን ይጠብቃል፡፡ ታዲያ የዚህ ሊቅ ንግግር ማስፈራሪያ ይመስለናል? በፍጹም አይደለም፡፡ ከዚህ ከንቱ ዓለም አስቀድመን ራሳችንን እንድናርቅ የሚያስጠነቅቅ በበረሃው ማንነታችን ላይ የሚጮህ ቀስቃሽ ድምጽ ነው፡፡
የተፈጠረበት ዓላማ የገባው ክርስቲያን ‹እግዚአብሔር ወደዚህ ዓለም ያመጣኝ ፤ መልሶ ገድሎ ከዚህ ዓለም ሊወስደኝ ነው!!!› እያለ በሞት ፍራቻ ተውጦ ፤ ራሱን ሲያስጨንቅና ፈጣሪውን ሲያማር አይውልም፡፡ ይልቅ አምላኩ ለኋለኛው የክብር ሕይወት ሊያዘጋጀው ወደዚህ ዓለም እንዳመጣውና ጊዜውም ሲደርስ ወደ ዋናው ተስፋ ሊያገባው በሞት ድልድይነት እንደሚያሻግረው ያምናል፡፡
መዝሙረኛው እንደዘመረው የሰው ልጅ በከንቱ የሚታወክ ፣ደግመው እንደማያገኙት ጥላ የሚመላለስ ፣ሊበትንም የሚያከማች ደካማ ነው (መዝ 39፡6)፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ይህን ሲገልጽ ‹ሰው በብዙ ነገር ይታወካል ፤ በፍጻሜው ግን ይጠፋል፡፡ ገና ሳይጀምር፤ ሁሉን ያጣል፡፡ እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እንደ ክሰልም ዓመድ ይሆናል፡፡ እንደ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል፤ እንደ ትቢያም ከመሬት ላይ ይቀራል፡፡ እንደ ነበልባል ይንቀለቀላል፤ እንደ ጢስ ደግሞ ይተናል፡፡ እንደ አበባ ይዋባል፤ እንደ ሳርም ይጠወልጋል፡፡ መታወኩ የእርሱ ነው፤ ደስታ ግን ወደ ሌሎች ይሄዳል፡፡ ጥንቃቄው የእርሱ ነው፤ ሐሴቱ ግን ወደ ሌሎች ይሻገራል፡፡› ሲል ይናገራል፡፡ ታዲያ ብዙ ጊዜ የደከምንበት ነገር ውጤት ምንድር ነው? የማይከተለንና ፈጥኖ የሚጠፋ ሥጋዊ በረከትን ብቻ ፍለጋስ ስለምን ጉልበታችንን አፈሰስን?
በዚህች ዓለም ሳለን የምንኩራራበት ባለጠግነት ፣የምንማረርበትም ማጣታችን ሁሉ ቀርቶ፤ የድህነትና የሃብት ጭንብላችንን አውልቀን አቻ የምንሆንበት ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ሚዛን ሳይዛባ እንደ ሥራችን እኩል የምንዳኝበት ሰዓትም በቶሎ ይመጣል፡፡ እስከዚያው ግን በእንግድነት ዘመናችን ለራሳችን እና ለሌሎችም የሚጠቅመውን መልካሙን ነገር ሁሉ እናድርግ፡፡

Audio
"ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን" ኤፌ 4፥7
➢ በውጭው አገር ለሚኖሩ አገልጋዮች ከሚሰጥ ተከታታይ ትምህርት ላይ የተወሰደ

+++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++
በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው።
ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን?
እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ ከሆነ ዘንድ ምን እፈልጋለሁ?" እንዳለን።(ሉቃ 12፥49) ይህ መድኃኒታችን በምድር ላይ የጣለው እሳት ምንድር ነው? አገልግሎቱስ እንዴት ነው?
ጌታችን በምድር የጣላት እሳት "ወንጌል" ትባላለች። ሰው ሰውነቱን ንጹሕና የተቀደሰ ሕያውም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብባት "የእግዚአብሔር እሳት" ወንጌል ነች። ይህች ወንጌል ጌታ አንድ ጊዜ በምድር የጣላት፣ እኛ ደግሞ ለዘወትር እንዳትጠፉ የምናቀጣጥላትና የምናነዳት እሳት ነች። የማቀጣጠያው እንጨቶችም ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እና ማንበብ ናቸው። ያለ ወንጌል እሳትነት ምንም መሥዋዕት እንድናቀርብ አልተፈቀደልንም። ነገር ግን እንደ አሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ ከመንደር ቆስቁሰን ወይም ራሳችን አቀጣጥለን የምናመጣቸው "ሌላ እሳት" የተባሉ ከንቱ ፍልስፍናዎችና እንግዳ ትምህርቶች የእግዚአብሔርን ቁጣ ይቀሰቅሱብናል።
ዳግመኛም እሳት የተባለው በጥምቀት ጊዜ በሁላችንም ላይ የወረደው ጸጋ እግዚአብሔር ነው። ይህም ጸጋ ለመዳናችን ዓይነተኛ ሚና አለው። ይሁን እንጂ ልክ በደብተራ ኦሪት እንደ ወረደው እሳት ካልተንከባከብነው እና ካላቀጣጠልነው ሊዳፈን እና የሌለ ሊመስል ይችላል። ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስ "እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው...በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ" በማለት የሚመክረው።(2ኛ ጢሞ 1፥6) እግዚአብሔር ለሰጠን ጸጋ ማቀጣጠያዎቹ ደግሞ ጾም፣ ጸሎትና መንፈሳዊ ትሩፋት ሁሉ ናቸው። እርሱ የሰጠህን የጸጋ እሳት ከማቀጣጠል ይልቅ "ሌላ እሳት" ላምጣ ያልህ ቀን ግን ታላቅ ጥፋት ያገኝሃል።

+++ "የመውጊያውን ብረት አንቃወም" +++
ቅዱስ ጳውሎስ ወደሚደነቀው የክርስትና ብርሃን ከመምጣቱ በፊት፣ ለአባቶች ወግ የሚቀና እና የአይሁድን ሥርዓት ከሁሉ ይልቅ አብልጦ የሚጠብቅ ሰው ነበር።(ገላ 1፥14) በክርስቲያኖች አፍ የሚጠራው "ኢየሱስ ክርስቶስ" የሚለው ስም ኦሪታዊው እምነቱን ያጠፋዋል የሚል ስጋት ስለ ነበረበት ክርስቲያኖቹን ያለ ልክ ያሳድዳቸው ነበር። በተለየ እነዚህ የክርስቶስ ተከታዮች በደማስቆ በሰላም እየኖሩ እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ ተቆጣ። እንደሚገድላቸውም እየዛተ በዚያ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ሊቀ ካህናቱ ገብቶ ለመነ።(ሐዋ 9፥1-2)
የጠየቀውንም ደብዳቤ እንዳገኘ ጊዜ ሳያጠፋ ወዲያው በፈረስ እግር እየፈጠነ ወደ ደማስቆ ገሰገሰ። ወደ ከተማው መግቢያ ሲቃረብ ግን ያላሰበው ነገር ተከሰተ። ከሰማይ የወጣ አንጸባራቂ ብርሃን አይኑን ወግቶ ጣለው። አስፈሪው ሳውል ከፈረሱ ላይ እንደ ነገሩ ወደቀ። ጌታ ሳውልን ገና በኢየሩሳሌም ሳለ ደቀ መዛሙርቱን ሲያሳድድበት እዚያው በብርሃን መትቶ አልጣለውም። ሳውል በክርስቲያኖቹ መካከል እያለ በብርሃን ቢመታ ኖሮ፣ አይሁድ ክርስቲያኖቹን እንደ አስማተኛ ቆጥረው ይከስሷቸው ነበር። ለዚህም ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ ሌላ ተገቢ ያልሆነ ስም ያወጡለት ነበር። ስለዚህ በደማስቆ ከተማ መግቢያው አፋፍ ላይ በብርሃን መትቶ ጣለው።
የጌታ አመጸኛን የሚስብበት ልዩ የሆነ የፍቅሩን ሰንሰለት ተመልከቱ። በብርሃን መትቶ ከጣለው በኋላ ያናገረው ግን "ስለ ምን ታሳድደኛለህ?" ("ምን አደረግኹ?") በሚል በሚለማመጥ ሰው ቃል ነበር። ልብ በሉ "አንተ ነህ እኔን የምታሳድደው?" አላለውም። ይህ የማስደንገጥና የቁጣ ቃል ነው። ቁጣ ብቻውን ደግሞ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያሠራም።(ያዕ 1፥20) ቢያሠራም የውዴታ አይደለም። ጌታ ግን ለአሳዳጁ ሳውል ያለውን ፍቅር በሚገልጥና ልብን በሚመረምር ቃል "ለምን ታሳድደኛለህ?" ሲል ጠየቀው።
በዚህ ፍቅሩም ምስኪን በጎቹን ለማጥቃት በአደገኛ ተኩላ ተመስሎ ሲበር የመጣውን፣ ከደማስቆ ደጃፍ ከከተማው በር አቅራቢያ ሲደርስ ተኩላነቱን አስጥሎ ከጎቹ መካከል እንደ አንዱ አደረገው። "ለምን ታሳድደኛለህ?" በሚለው ቃል ገዳዩ ሳውልን ጥሎ፣ በጎቹን የሚጠብቅና ስለ እነርሱም ሲል የሚሞት "እረኛው ጳውሎስ"ን አስነሣው።
ሳውል የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያሳድድ የነበረው ከክፋት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ከነበረው ቅናት የተነሣ ነው። አሳዳጅነቱም የእውነት ጠላት ከመሆን ያይደለ፣ አምላክን አገለግላለሁ ከሚል የዋሕ አሳቡ የተወለደ ነበር። ስለዚህ የየዋሐን ሰዎች የክፋት ጽዋ ስትሞላ ተገስጸው ይማሩበታል እንጂ አይጠፉበትምና፣ እግዚአብሔር የዋሑ ሳውልን መገሰጽን ገሰጸው፤ ለሞት ግን አሳልፎ አልሰጠውም ።
ሳውል "ለምን ታሳድደኛለህ?" የሚለውን ድምጽ በሰማ ጊዜ፣ "ጌታ ሆይ ማን ነህ?" ሲል ጠየቀ። ጌታም "አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" አለው። የአንድ ሕዋስ መታመም ለአካሉም ጭምር ይተርፋል። እጅ በስለት ቢወጋ አፍ ደግሞ ይጮሃል። ምእመናንም የክርስቶስ አካል በተባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ያሉ ሕዋሳት ስለሆኑ፣ እነርሱን ማሳደድ ክርስቶስን ማሳደድ ነው። ስለዚህም መድኃኒታችን ራሱን በክርስቲያኖች ቦታ አስገብቶ "የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ" አለው።
"የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" የሚለውን ቃል ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ልክ እንደ እንቆቅልሽ ያለ ንግግር እንደ ሆነ ጽፈዋል። "የመውጊያ ብረት" የሚለውን የኢትዮጵያ ሊቃውንት "ሰይፍ" ብለው ተርጉመውታል። ኃይለ ቃሉን ሲያብራሩትም "ሰይፍን የረገጠ ሰው እርሱ ይጎዳል እንጂ ሰይፋ ምንም አይሆንም። አንተም ከእንግዲህ ወዲህ ምእመናንን ብታሳድድ ለእነርሱ ስደቱ ክብር ስለሆነ ይጠቀሙበታል። አንተ ግን ሳትጎዳበት አትቀርም" ሲለው ነው ይሉናል። ግሩም ትርጓሜ!
ከዚህ በተጨማሪ "የመውጊያ ብረት" ፈረስ የሚጋልብ ወይም በሬ የሚጠብቅ ሰው የሚገለገልበት መሣሪያ ነው። ገበሬዎችና ፈረስ ጋላቢዎች ፈረሱ ፍጥነት ሲቀንስባቸው፣ በሬውም አልሄድም ብሎ ሲለግምባቸው ሁለቱንም "በመውጊያው ብረት" እየወጉ ያነቁበታል። ቃለ እግዚአብሔርም የመውጊያ ብረት ነው። ሳውል ቀድሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ በኩል የሰማውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ብሎ ነበር። የቆመበትን አይሁዳዊነት ለቅቆ ወደ ክርስትናው እንዲሻገር የሚያነቃውን የመውጊያ ብረት ተቃውሞ ነበር። ስለዚህም ጌታችን አሁን "የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ሲል አስጠነቀቀው።
ከቆምንበት የኃጢአተኞች መንገድ፣ ከተቀመጥንበት የዋዘኞች ወንበር ቀስቅሶ የሚያነቃንን "የመውጊውን ብረት" ቃለ እግዚአብሔር አንቃወም። ልባችን አይደንድን፣ የቤተክርስቲያንን ድምጽ እንስማ።
"የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል"
ዕብ 4፥12

ኃጢአት የሌለበትን በዚህ ዓለም ያለውን ደስታ ለማግኘት መንገዱ ቀላል ነበር። ሁሉም ሰው በሕይወቱ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር የሚያስችለውን በቂ ምክንያት ቢፈልግ ከእጁ አያጣውም ነበር። ነገር ግን ሰው የማይቆም ፉክክር ውስጥ ራሱን ስላስገባ የእርሱ "ደስታ" አጠገቡ ካለው ጎረቤቱ ወይም ባልንጀራው ካልበለጠ ደስ አይለውም። ይህም በሌላ መንገድ ሲገለጽ ከጎኑ ያለው ወዳጁ ካልተከፋ ወይም ካላዘነ እርሱ መቼም ቢሆን ደስተኛ አይሆንም ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ፊትህ በደስታ እንዲበራ መልካሙን አድርግ ሲል ይመክረናል። የእኛ ፊት ግን የሚበራው በወንድሞቻችን መከፋት ነው። ደስታን በመፈለግ ውስጥ ያለብንን ክፋት ተመልከቱ?! በሌሎች ቁስል ላይ የሚመሠረት ይህ ደስታ ሰይጣናዊ ነው። ፍጻሜውም ኃዘንና ጥርስ ማፏጨት ካለበት ሲኦል የሚያስጥል ነው።
በሌላው ሙሾ ውስጥ ደስታን የመፈለግ አባዜ ሥነ ልቡናዊ ቀውስም ጭምር እንደ ሆነ የዘርፉ ሊቃውንት ይናገራሉ። በተለይ ለራሳቸው አሉታዊ የሆነ አመለካከት (low self-esteem) ያላቸው ሰዎች "ሻደንፍሩይድ"/"Schadenfreude" በተባለው በዚህ ክፉ የአእምሮ ምስቅልና ይጠቃሉ።
ይህ ደዌ አሁን አሁን የሁሉም ሳይሆን አልቀረም። የተማሪው፣ የነጋዴው፣ የቢሮ ሠራተኛው፣ የዘማሪው፣ የሰባኪው...የሁሉም
እንግዲህ ምን እንላለን? የሰማዩ ባለመድኃኒት እርሱ ይፈውሰ እንጂ!
"አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ" መዝ 51፥10