YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ''ሚዲያ እና ዴሞክራሲ'' በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተከበረ ነው። #WorldPressFreedomDay

@YeneTube @FikerAssefa
በፕሬስ ነጻነት ከኢትዮጵያ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

ምስላዊ መረጃ፦ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (RSF) በየዓመቱ የ180 ሀገራትን የፕሬስ ነጻነት በመመዘን ያስመዘገቡትን ደረጃ ይፋ ያደርጋል። ድርጅቱ በትላንትናው ዕለት ባወጣው የዘንድሮው ዝርዝር ኢትዮጵያ 145ኛ ደረጃ አግኝታለች። ይህ ውጤት ሀገሪቱ አምና ከነበረችበት በአራት ደረጃዎች መውረዷን ያመለከተ ሆኗል።

በድርጅቱ ዝርዝር መሰረት የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ዘንድሮም “በጣም አሳሳቢ” በሚባለው ውስጥ ምድብ ውስጥ የሚገኝ ነው። ከዓለም ህዝብ ከግማሽ በላይ የያዙ 42 ሀገራት በዚሁ ምድብ ውስጥ የሚገኙ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል። እነዚህ ሀገራት የጋዜጠኝነት ሙያን መተግበር “አደገኛ የሆነባቸው” አሊያም ደግሞ የፕሬስ ነጻነት “ከእነአካቴው የሌለባቸው” እንደሆኑ ድርጅቱ ገልጿል።

ኢትዮጵያ በRSF ዝርዝር የመጨረሻዎቹን ደረጃ ከያዙ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ውስጥም ተካትታለች። ኢትዮጵያን ተከትላ በ146ኛ ደረጃ የተቀመጠችው ሩዋንዳ ናት። ሁለቱ የኢትዮጵያ ጎረቤቶች ሱዳን እና ጅቡቲ እንደ ቅደም ተከተላቸው 156ኛ እና 168ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ግብጽ 170ኛ ደረጃን አግኝታለች። ሌላኛዋ የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤርትራ እንደ አምናው ሁሉ በድርጅቱ ዝርዝር የመጨረሻውን 180ኛ ደረጃ ይዛለች። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

#WorldPressFreedomDay
👍17😭54