YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ብቻ በ27 አለማቀፍ ከተሞች ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ አደረጉ!

በአለማቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በ27 ከተሞች የአሜሪካ መንግስት እና አንዳንድ የምእራባዊያንን መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ነጩ ቤተ መንግስት በርካቶች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል።

የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ የኢትዮጵያን መንግስት በሀይል ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል።ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በቃ በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ በርካቶች በተካፈሉበት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን የአፍሪካ የነጻነት አርማነቷን፣ ወራሪዎችን አሳፍራ የመለሰች የጀግኖች አገር መሆኗን ፣ከጥቁር ህዝቦች በብቸኝነት በቅኝ አገዛዝ ጥላ ስር ያልወደቀች አገር መሆኗን በማስታወስ አሜሪካ የተሳሳተ ፖሊሲዋን ከማራመድ እንድትቆጠብ ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።የህወሓት ቡድንን መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዚደንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
“በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም" በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ!

"ሰላም ይስፈን በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም" በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ስለመሆኑ ኢብኮ ዘግቧል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የደረሰውን ጥቃት በማውገዝ ላይ ናቸው።

የውጭ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ እያደረሱ ያለውን አግባብ ያልሆነ ጫና እና ጣልቃ-ገብነትን በመቃወምም #NoMore የሚል መፈክር እያሰሙ ነው።በሰልፉ ላይ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና በርካታ ሕዝብ እየታደመ ይገኛል።

@YeneTube @FikerAssefa
በመዲናዋ በነገው ዕለት ሊካሄድ የነበረው የ “በቃ” ሰልፍ ለቀጣይ ሳምንት ተላለፈ!

በአዲስ አበባ በነገው ዕለት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የ “በቃ” ወይም #Nomore ሰልፍ በዳያስፖራው ጥያቄ መሰረት ለቀጣይ ሳምንት መተላለፉ ተገለፀ፡፡በርካታ የዳያስፖራው ማህበረሰብ አሁንም ወደ አገሩ እየገባ በመሆኑ ሰልፉ ቀጣይ ሳምንት የሚካሄድ መሆኑን ነው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላከተው፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ዲፕሎማሲያችን ከየት ወደየት በኤልያስ መሰረት ታዬ ሲቃኝ።

ኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ልዕልና ካላቸው ሀገራት አንዷ ነች፣ ከኒውዮርክ እና ጄኔቫ ቀጥሎ የአለም ትልቋ የዲፕሎማሲ መቀመጫ መሆኗ አንዱ ምስክር ነው።

በሊግ ኦፍ ኔሽን መላው የጥቁር ዘርን ወክለው ሲሞግቱ የነበሩት ቀዳማዊ አፄ ሀይለ ሥላሴ የሞኖሮቪያ እና ካዛብላንካ ተፃራሪ አሰላለፎችን አስማምተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት) በሀገራችን መቀመጫውን እንዲያደርግ አስችለዋል።

ከዛ ወዲህም ይሁን ከዛ በፊት የነበሩ መንግስታትም ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ልዕልናዋ ያለበትን ደረጃ በደንብ አሳይተዋል።

ከሰሞኑ የዲፕሎማሲ ባዛር በመዲናችን ተከፍቷል፣ "ከአፍሪካ መዲና እስከ አለም መድረክ" በሚል ስያሜ በርካታ መረጃዎች ለህዝብ እየደረሱ ነው። ታድያ በዚህ አጋጣሚ ዲፕሎማሲያችን አሁን ላይ ያለበትን ቦታ በአጭሩ በራሴ እይታ ለመቃኘት ፈለግሁ።

ኢትዮጵያ ከጎረቤቷ ኤርትራ ጋር ያለባትን ችግር በሰላም ፈትታ ግንኙነት መፍጠሯ ትልቅ የቅርብ ግዜ ስኬት ነበር። ይህ የዲፕሎማሲ እምርታ የኖቤል ሽልማትን ለጠ/ሚር አብይ አህመድ አስገኝቷል። ከዛ በኃላም በጠ/ሚሩ መሪነት ኢትዮጵያ፣ ሶማልያ እና ኤርትራ የጋራ ፎረም መስርተው ቀጠናውን እፎይ አሰኝተው ነበር።

ትንሽ ቆይቶ ግን ደም አፋሳሹ የሰሜኑ ጦርነት ሲከሰት መንግስት የሄደበት 'ይህም ጠላቴ፣በ ያም ጠላቴ' አካሄድ ከበርካታ ሀገራት እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ያልተገባ ቅያሜ እና ንትርክ ውስጥ ከቶታል። በ #NoMore ሀሽታግ ያደጉ ሀገራት ሲወቀጡ 'እንገዳደልበት፣ እናንተ አያገባችሁም' አካሄድ መስሎ ነበር። ውጤቱን በኋላ አይተነዋል።

በመጨረሻ ግን ጦርነቱ በስምምነት ሲጠናቀቅ እነዚሁ አያገባችሁም የተባሉ የዲፕሎማቲክ አጋሮች ፊርማ አፈራራሚ እና የወደመውን ገንቢ ሆነው ተመልሰዋል፣ ዲፕሎማሲው እና ኢኮኖሚው ላይ የደረሰው ኪሳራ ግን ከባድ ነው፣ ኢትዮጵያ እስካሁን ከአጎዎ ታግዳ እንዳለች ልብ ይሏል።

የኤርትራ ወታደሮችን አስውጡ ሲባል "የኤርትራ ወታደር የለም"፣ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ "አሉ ግን ጥፋት ካለባቸው እናጣራለን"፣ ሲለው ደግሞ የበርካታ ድርጅቶችን ስም በማጥፋት የተጠመደ አሰራር ነበር። የተመድ ዋና ፀሀፊ በአንድ ወቅት በድርጅቱ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ንግግር በአንድ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ላይ ማድረጋቸው የቅርብ ግዜ ትውስታ ነው።

አሁን ከሰሞኑ ደግሞ የወደብ ጉዳይ ከተነሳ ጀምሮ ዲፕሎማሲው እጅጉን እየተፈተነ ነው። ኤርትራ አኩርፋ ፊቷን አዙራለች፣ ሶማልያ ከኢትዮጵያ ጋር አንድ ሁለት እየተባባለች ነው፣ የሱዳን ሉኡላዊ ምክር ቤት በግልፅም ከጀርባም ኢትዮጵያን ይከሳል፣ ብዙ አይነገርም እንጂ ከኬንያ ጋር ያለው ግንኙነትም የቀድሞ ቦታው ላይ አይደለም። የአፍሪካ ልማት ባንክ ሰራተኞች ላይ የደረሰው ድብደባ እና እስርም ትልቅ የዲፕሎማሲ incident ሆኖ ተመዝግቧል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በትናንትናው እለት እንዳሉት "ይሄንን ፊርማ (ከሶማሌላንድ ጋር) እስክንፈርም ድረስ በUN ተቋማትም፣ በአንዳድን ትላልቅ ሀገሮች የመረጃዎችም፣ በእኛ Think Tank በሚባሉ NGOዎችም ይሰራ የነበረው ጥናት የኢትዮጵያ መንግሥት ወይ ኤርትራን ይወራል፣ ወይ ደግሞ ሶማሌላንድን በአውዳል ግዛት በኩል ረብሻ ፈጥሮ ቀጠናውን ያተራምሳል የሚል ጥናት ነበር ሲሰራ የነበረው" ብለዋል።

ግን ዋናው ጥያቄ ኢትዮጵያ እንዲህ ለምን ተገመተች? ርዋንዳ፣ ኮንጎ፣ ኮርያ፣ ሶማልያ... ወዘተ ጦሩን እየላከ ለአለም የተረፈ ሀገር ለምን እንዲህ ችግር ፈጣሪ ተደርጎ ተሳለ?

ይህ ትልቁ ጥያቄ ነው።

ከሁሉም አሳሳቢው ግን ኢትዮጵያ ለሶማልያ ተገንጣይ ግዛት ሱማሌላንድ እንደ ሀገር እውቅና ልሰጥ አስቤያለሁ ማለቷ ጉዳዩ ከአሜሪካ እስከ ቻይና፣ ከሳውዲ አረቢያ እስከ ቱርክ ተቀባይነትን አጥቷል። ኢትዮጵያ ላይ ቅያሜ ያለው ሀገር ሁሉ በድብቅ እና በግልፅ እየተገናኘ መዶለት ጀምሯል።

መቼም ኢትዮጵያ ወደብ ቢኖራት ደስ የማይለው ካለ ችግር አለ ማለት ነው፣ ነገር ግን በአሳዛኝ ሁኔታ ያጣነውን ወደብ ሀገርን ለአደጋ በሚያጋልጥ፣ አለም አቀፍ ህግጋትን በሚጥስ እና ሀገር ውስጥ ያለውን ግጭት ይበልጥ ሊያፋፍም በሚችል መልኩ መደረጉን ደግሞ መተቸት ትክክል ይመስለኛል። እርግጥ ነው ግርርርር... ብሎ የሚከተል ካድሬ ሁሉ አንዳንድ አካሄዶችን ሲጠይቅ "ባንዳ" ምናምን እያለ ለማሸማቀቅ መሞከሩ አይቀርም።

አሁንም ዋናው ጉዳይ ለኢትዮጵያ መቆርቆር ማለት በመንጋ መጓዝ ብቻ ሳይሆን የመንግስት አካሄድ መንገድ ሳት ያለ ሲመስለው "ለምን?" ብሎ የሚጠይቅ ዜጋ፣ ዲፕሎማት እና ፖለቲከኛ ነው።

ተፃፈ በ EliasMeseret
@Yenetube @Fikerassefa
👍116👎1810