ኢ/ር ታከለ ኡማ ከትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተዋል፡፡
-
ኢ/ር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ከነሃሴ 12 ጀምሮ የተገበራቸውን አዳዲስ አሰራሮችን በቦታው በመገኘት ምልከታ አድርገዋል፡፡
የቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት ከነሃሴ 12/2011 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት አዳዲስ ስራዎችን ተግባራዊ አድርጓል፡፡
የባቡር ትራንዚት አገልግሎቱ ለተጠቃሚዎች ወጥ የትኬት ዋጋ እንዲሆን እና ከዚህ በፊት የነበረውን የዋጋ ልዩነት አስቀርቶ ተገልጋዮች ወጥ ዋጋ ከፍለው አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም የህዝብ ምልልሱን ለማቀላጠፍ የባቡር የጊዜ ሰሌዳን (Timetable) ወደ 10ደቂቃ ዝቅ በማድረግ በፍጥነት ህዝብ ለማመላስ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የትራንስፖርት ሚንስተር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በባቡር ጣቢያ በመገኘት አዲስ የተተገበረውን አሰራር ተመልክተዋል፡፡
አገልግሎቱን ከዚህ በተሻለ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ለማድረግ እና ሊተገበሩ በሚገቡ ስራዎች ዙሪያም ምክክር አድርገዋል፡፡
#Mayor office
@YeneTube @FikerAssefa