YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቤት እየፈረሰ ነው!

• አራት ልጆቼን ይዤ ጎዳና ላይ ወድቂያለሁ
• ከ 3ሺህ 685 ሕገወጥ ቤቶችን እያፈረስኩ ነው - የለገጣፎ ከንቲባ ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ

ለገጣፎ የካ ዳሌ ሠፈር ‹‹አካባቢው ለጤና ተቋማትና ለትምህርት ቤት መስሪያ ይፈለጋል›› በሚል ምክንያት የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ ነው፡፡

የለገጣፎ አስተዳደር፤ ከንቲባ ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - በዚህ ሳምንት 3 ሺህ ቤቶች እንደሚያፈርስ እና በቀጣይም 12 ሺህ ሕገ ወጥ ቤቶች መኖራቸውን እነርሱም መፍረሳቸው አይቀርም ሲል ለ#OMN ተናግረዋል።

የአራት ልጆች እናት እንዲህ አለች …

‹‹ሕጋዊ ነን፡፡ የአፈር መሬት ግብር 97/98 ዓ.ም. ገብረናል፡፡ መብራት እንዲሁም ዉሃ ገብቶልናል፡፡ … የቤት ቁጥርም ተሰጥቶናል፡፡ ይሄው ተመልከተኝ አራት ልጆቼን ይዤ ጎዳና ላይ ወድቂያለሁ፡፡ ከመኖሪያ ቤታቸን አፈናቅሎ ቦታው ለ #Green Area ይፈለጋል ማለት ምን ማለት ነው? … መንግስት ‹‹ዜጎችን ከጎዳና እያነሳሁ ነው›› እያለ ከነልጆቼ ወደ ጎዳና መወርወር ምን ማለት ነው?›› በእንባ እያፈሰሰች …

ምንጭ:- ጌጡ ተመስገን
@YeneTube @FikerAssefa