YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#CoupAlert

በማይናማሯ መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተፈፀመ!

በቀድሞዋ በርማ በአሁኑ መጠሪያዋ ማይናማር የምትባለው ሀገር መሪ ዳው አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ መፈንቅለ መንግስት እንደተፈፀመባቸው እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎች ያሳያሉ። የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የተቋረጠ ሲሆን የኢንተርኔት እና የስልክ ግኑኝነት በተመሳሳይ ተቋርጠዋል። መከላከያ ሰራዊቱ በራሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳስታወቀው ከሆነ በሀገሪቱ ለአንድ አመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ይህንንም ተከትሎ ሁሉም ስልጣኖች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ እንደሚሆኑም ተገልጿል። በዚህ መግለጫ መሪዋና የሷ ሰዎች ከሁለት ወር በፊት የተደረገውን የምርጫ ውጤት በማጭበርበራቸው ከስልጣን እንዲነሱና እንዲታሰሩ ተደርገዋል በሚል ተገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa