YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኮሚሽኑ የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ!

ኢትዮጵያ በታላቅ ድምቀት የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት በቂ ዝግጅት በማድረግ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በሃገሪቱ በየዓመቱ የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይደሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንደኛው መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡

ይህ ታላቅ በዓል በመላው ኢትዮጵያ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሀይማኖታዊ በዓል ከመሆኑም በላይ የቱሪስት መስህብ በመሆን የሃገሪቱን መልካም ገፅታ በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚና አለው ብሏል፡፡

በዓላቱ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር የፌዴራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት በቂ ዝግጅት በማድረግ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ #ፌዴራል_ፖሊስ _ኮሚሽን አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa