ጎንደር🔝
የጥምቀት በዓል ከመድረሱ በፊት የማዕከላዊ #ጎንደር ዞን የባሕል ሳምንት ያካሂዳል፡፡ የባሕል ሳምንቱም የአካባቢውን ትውፊታዊ ማንነት እና አጋጊያጥን ጨምሮ ለጎብኝዎች በጎዳና ላይ ትርኢት ያሳያል፡፡
የጎዳና ላይ ትርኢቱም የጥምቀት በዓል ከመከበሩ በፊት የሚካሄድ በመሆኑ የአካባቢውን ባሕል በአምባሳደሮቹ አማካኝነት ፍንትው አድርጎ በማሳየት ትልቅ ሚና እንደተወጣም ተነግሯል፡፡ ስምንተኛው የባህል ሳምንት ፌስቲባል በጎንደር ከጥር 7 እስከ 9/2011 ሲከበር ቆይቶ ከማዕከላዊ ጎንደር የተወጣጡ የባሕል አምባሳደሮች ዛሬ ትርኢታቸውን በጎዳና ላይ በማቅረብ አጠናቅቀዋል፡
ምንጭ፦ አብመድ
@YeneTube @Fikerassefa

በአማራ ክልል ሰሜን #ጎንደር_ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት በነበሩ ግጭቶች #90_ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን የአውሮፓ #ኮሚሽን አስታወቀ። ከተፈናቃዮቹ ውስጥ 40 ሺህ የሚሆኑት በቅማንት እና በአማራ ብሔር ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ምክንያት ቀያቸውን የለቀቁ ናቸው ብሏል ኮሚሽኑ።
በኮሚሽኑ የሲቪል ጥበቃ እና የሰብዓዊ ርዳታ ተልዕኮ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ትላንት ባወጣው መግለጫ በሰሜን ጎንደሩ ግጭት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና የበርካታ ቤቶች ቃጠሎ እንደነበር መዘገቡን ገልጿል። የአማራ ክልል በአካባቢው የተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ከአቅሙ በላይ መሆኑን ከሳምንት በፊት ማስታወቁን እና የሰብዓዊ ርዳታ አቅራቢዎችን ድጋፍ መጠየቁን መግለጫው ጠቁሟል።
በአማራ ክልል ጥያቄ መሰረት አስራ ስምንት ሺህ አባወራዎችን ለመርዳት 18 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል። የአውሮፓ ኮሚሽን በበኩሉ በቅርቡ የተካሄዱ የሰብዓዊ ጉዳይ ዳሰሳዎች ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ አንገብጋቢ መሆኑን አመላክተዋል ብሏል። ተፈናቃዮቹ እንደ ምግብ፣ መጠለያ እና ከመብል ውጭ ያሉ ሌሎች የመሰረታዊ አቅርቦት ቁሳቁሶች በአስቸኳይ እንደሚያስፈልጓቸው አትቷል።
በሰሜን ጎንደር የቅማንት ብሔር ተወላጆች የራስ ገዝ አስተዳደርን ከመጠየቃቸው ጋር በተያያዘ በአካባቢው ከ2009 ዓ. ም ዓመት ወዲህ ውጥረቱ እያየለ መምጣቱን የአውሮፓ ኮሚሽን መግለጫ አስታውሷል። በአካባቢው ከህዳር 2010 ዓ. ም ወዲህ በተለይ ሁከት እና መፈናቀሎች መከሰታቸውን ጠቅሷል። በዚህም ምክንያት ከአንድ ሺህ የሚልቁ የቅማንት ተወላጆች ወደ ሱዳን መሰደዳቸውን እና ከእነርሱም ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩት ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጿል።
በአማራ ክልል በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር የተከሰተውን የጸጥታ መድፍረስ ለመቆጣጠር ከሁለት ሳምንት ወዲህ የመከላከያ ሰራዊት በአካባቢዎቹ እንዲሰማራ መደረጉ ይታወሳል። የክልሉ መንግስት ከጎንደር እስከ መተማ በተዘረጋው አውራ ጎዳና እና ከጎንደር ወደ ሁመራ በሚወስደው መንገድ በአምስት ኪሎ ሜትር ክልል በግልም ይሁን በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስም ከልክሏል።
ምንጭ:-Dw
@YeneTube @FikerAssefa