YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ከ #ኢትዮጵያ እና ከ #ጂቡቲ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ቃል ገቡ!

የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን ሞሀመድ አብዱላሂ ኢሮ ከኢትዮጵያ እና ከጂቡቲ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ቃል ገቡ። ፕሬዝዳንቱ ግኙኝነቱ የሶማሊላንድ ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ ጸጥታ እና ቀጠናዊ ትብብርን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታ እንዳላቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሮ እሁድ እለት በሀርጌሳ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ወሳኝ ጎረቤት እና የረጅም ጊዜ አጋር መሆኗን አሞግሰዋል። "ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየ ወዳጅና በኢኮኖሚ ልማት፣ በጸጥታ እና በአፍሪካ ውስጥ ግንኙነታችንን በማጠናከር ረገድ ወሳኝ አጋር ናት" ብለዋል። "ይህንን ግንኙነት እና የጋራ ጥቅሞቹን ማጎልበት ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉም አክለዋል።

በተጨማሪም ሶማሊላንድ ከጂቡቲ ጋር ያላትን የቀዘቀዘ ግንኙነት መልሶ ለመገንባት እና ከአሜሪካ ጋር ትብብርን ለምጠናከር ተስፋ እንዳላት ገልጸዋል። “በሶማሊላንድ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ካሳዩ ሁለት ሀገራት ማለትም ከጂቡቲ እና ከአሜሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት እናጠናክራለን" ማለታቸውን ሂራን ዘግቧል።

ባሳለፍነው አመት በሶማሊላንድ የቀድሞ ፕሬዝዳንት እና በጠ/ሚ አብይ አህመድ( ዶ/ር) መካከል ለሶማሊላንድ እውቅና ለኢትዮጵያ ደግሞ የባህር በር የሚያስገኝ የመግባባቢያ ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በስምምነቱ ደስተኛ ካልሆነችው ሶማሊያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት በቅርቡ በአንካራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የመግባቢያ ስምምነቱ ትግበራ ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።ከሶማሊያ ባለሥልጣናት በኩል ይህ የመግባቢያ ስምምነት እንደተሻረ ቢናገሩም ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር የለም።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
👍2416😁2🔥1