YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ጎንደር ዩንቨርስቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተወሰደ እርምጃ!

"በዩኒቨርሲቲያችን በተከሰተው አለመረጋጋት የመማር ማስተማር ሂደቱ ሲቆራረጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡በዚህም መሰረት በዩኒቨርሲቲው ሰላም እንዲሰፍን፣ ዩኒቨርሲቲው ሲሰራቸው ከቆየው ሰፊ ተግባራት በተጨማሪ ከፌደራል መንግስት የተላኩ ልዑካን በዩኒቨርሲቲያችን ውስጥ ከሚገኙ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ከከተማው ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ሰፊ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በእነዚህ ውይይቶችም አንዳንድ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሙያ የተከሰተውን ሁከት በማነሳሳት፣ የህይዎት እና የአካል ጉዳት እንዲደርስ በተለያዩ ደረጃዎች አሉታዊ አስተዋፅኦ በማድረግ በተደጋጋሚ ምክር ቢሰጣቸውም ችላ በማለት ተማሪዎች ክፍል እንዳይገቡ ክልከላ በማድረግ እና ትምህርት እንዳይጀመር ተማሪዎችን እና መምህራንን በማስፈራራት፣ ስለት ነገሮችን ግቢ ውስጥ ይዘው በመገኘት፣ አደንዛዥ እፆችን በመጠቀም እና ይዘው በመገኘት፣ ሃላፊነትን ባለመወጣት በሰራ ቦታቸው ላይ ባለመገኘት እና ችግሩ ሲከሰት ሪፖርት ባለማድረግ ሁከት እንዲስፋፋ በማሰብ ሰራተኞችን በማነሳሳት እና ቀስቃሽ መልእክቶችን በመበተን ተሳታፊ ሲሆኑ መቆየታቸውን መረዳት ተችሏል፡፡በመሆኑም ታህሳስ 22/2012 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በተለያየ ደረጃ ተሳታፊ ሆነው በተገኙ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና የጤና ባለሙያ ከቀላል የፅሁፍ ማሰጠንቀቂያ እስከ ሙሉ በሙሉ ከስራ እና ከትምህርት የማሰናበት እርምጃ ወስዷል፡፡

በዚህም 2 ተማሪዎች አንድ አመት ከትምህትር ገበታቸው #እንዲታገዱ፣ 39 ተማሪዎች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ እንዲሁም 11 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታቸው(ከዩኒቨርሲቲው) እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ለ7 መምህራን ቀላል #የጽሁፍ_ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ ለ3 መምህራን እና ለ8 የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ባለሙያ ሙሉ በሙሉ #ከስራ_እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡ወደፊትም ትምህርት የመማር ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች መብት ለማስጠበቅ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲያችንም ሆነ የከተማችን ማህበረሰብ ሰላም ለማስከበር በመሰል ድርጊቶች ሲሳተፉ በሚገኙ ተማሪዎች፤ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድ ሴኔቱ በጥብቅ አሳስቧል፡፡"

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa