YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኦሞ ወንዝ ባስከተለው የውሃ መጥለቅለቅ 15 ሺህ ሰዎች ተፈናቀሉ

በደቡብ ክልል የሚገኘው የዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝ ውሃ በመጥለቀለቁ፤ 15 ሺህ ገደማ ሰዎች መፈናቀላቸውን የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ አስታወቀ። ወንዙ ባስከተለው ጎርፍ 15 ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በሌሎች ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱንም ገልጿል።

የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዩች መምሪያ ኃላፊ አቶ መላኩ ለማ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት የኦሞ ወንዝ ላስከተለው የውሃ መጥለቅለቅ መንስኤው #የግልገል_ጊቤ ሶስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከመጠን በላይ በመሙላቱ የተለቀቀ ውሃ ነው። በዚህም ምክንያት በዳሰነች ወረዳ ከሚገኙ 40 ቀበሌዎች ውስጥ ሃያ ስምንቱ በዚህ ሳምንት በወንዙ መጥለቅለቃቸውን አስረድተዋል።

Via:- ethiopiainsider
@Yenetube @Fikerassefa