በትግራይ የሚገኙ የተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አምባሳደር ማሲንጋ አስታወቁ፣ ከህወሓትና ከሰራዊቱ አመራሮች ጋርም መክረዋል
በትግራይ የሚገኙ የተፈናቃዮች ጉዳይ ግዜ የማይሰጠው እና አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው በመሆኑ ወደ ቀያቸው ለመመለስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ በኢትዮጵያ #የአሜሪካን አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ አስታወቁ፤ ከህወሓትና ከሰራዊቱ አመራሮች ጋርም መምከራቸው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ማሲንጋ ትላንት ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በሽሬ የሚገኙ የተፈናቃይ መጠለያ ካምፖችን ጎብኝተዋል፤ “ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ዘላቂ መፍትሄ አይደለም፣ ዘላቂው መፍትሔ በአፋጣኝ ተፈናቃዮቹ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል”።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኒኤል አሰፋ በበኩላቸው ከአምባሳደር ማሲንጋ እና ልዑካቸው ጋር የተደረገው ውይይት ዋና ትኩረታችን በተፈናቃዮች መመለስ ላይ ነበር ብለዋል።
“ከአንድ ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች በልመና መልክ ከሚገኝ ድጋፍ ከማኖር እነዚህ አንድ ሚሊየን አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች እያረሱና እየነገዱ ወደሚኖሩበት ቀያቸው መልሶ ማኖር ነው የሚቀለው፤ ስለዚህ ዋነኛ መፍትሔው የዚህ ጉዳይ ወደ ቀያቸው መመለስ መሆኑን አስምረንበታል” ብለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7832

👍18❤4😁2