YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር #ዐቢይ አህመድ በ11ኛው የግንባሩ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር #የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች ፡-⤵️⤵️⤵️

• 11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ በለውጥ ምሁዋር ውስጥ በገባንበት ወቅት መካሄዱ ታሪካዊ ያደርገዋል፡፡

• ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች እያሸነፈ እንደመጣው ሁሉ የሚገጥሙትን ችግሮች እየፈታ የለውጡ ሞተር ሆኖ አገር መምራቱን ይቀጥላል፡፡

• ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ነገዋን በመፈለግ ላይ ያለች፣ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች አገር ናት፡፡

• የሽግግር ሂደቱን የአገራችን አርሶአደር “የበሬውን ብልሃት እና የወይፈኑን ጉልበት አቀናጅቶ” …እንደሚለው ሁሉ በእኛም ዘንድ ተተኪዎችን በጎ ልምድ ካላቸው በማስተሳሰር አገራዊ ለውጡን ለማሳካት ኢህአዴግ ይታትራል፡፡

• አገር የምታድገው በቅብብሎሽ ነው፡፡

• ያለትላንት ዛሬ አልተገኘምና የትናቱን ትውልድ ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ እኛም በተራችን በተተኪ ትውልድ መተካታችን አይዘነጋምና፡፡

• መተካካት የታቀደ ሂደት እንጂ ድንገተኛ ሆኖ እልቂት እንዳያመጣ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

• ይህ ትውልድ ስልጣንን በእጁ አስገብቶ ቀድሞ የነበረውን ነገር በማስፍረስ የተጠመደ መሆን አይገባውም፡፡

• ትላንት እና ዛሬን ያጣጣመች ኢትዮጵያን ለመገንባት ተግቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡

• ኢትዮጵያ በላቀ ተግበራቸው ያገነኗት መሪዎች እንደነበሯት ሁሉ፣ ውድቀት የዳረጓትም ነበሩ፡፡ ለጠላቶቿ የሰጧት መሪዎችም ነበሩ፡፡

• ያለመተማማን በማስፋት፣ በጠብና በጦርነት ሊተላለቁ የነበሩ ልጆቿን አስታርቀው ወደ ልዩ ምዕራፍ ያስገቧት ነበሩ፡፡

• በአሁኑ ጊዜ ያለው አመራርስ የትኛውን ታሪክ ይደግማል? የሚለው ጥያቄ ለእኛ ቀርቧል፡፡

• የአገራችን እጣ ፈንታ አሁን እድሉን ባገኙት ፖለቲከኞች እንዲሁም በህዝቧ እጅ ነው፡፡

• ዘመናዊና ስልጡን አገር ለመፍጠር ህዝብን የስልጣን ልዕልና መገለጫ አድርጎ የሚቀበል ስርዓት መፍጥር ሲሳካልን ነው፡፡

• ህዝብ የሚያምናቸውና የሚከተላቸው ልዩ ልዩ የማህበረሰብ መሪዎችን ካገኘን በእምነት፣ በባህል፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፖለቲካ፣ በጦር አመራር፣ በምህንድስና፣ በስፖርትና ኪነጥበብብ፣ በሌሎች ዘርፎችም ጭምር ከተዋጣልን አገር የተሳካ ጉዞ አድርጋ በከፍታ ጉዞ ላይ ትደርሳለች፡፡

• የምንፈልጋትን አገር መምሰልና መሆን የሚገባን እኛው ራሳችን ነን፡፡

• የበለፀገች የጋራ ቤታችንን ለጋራ ልጆቻችን ማድረስ የምንፈልግ ከሆነ ዝርፊያውንነና መጠላለፉን ትተን በጋራ መስራት አለብን፡፡

• ዘርና ሀይማኖትን መሰረት አድርገን ሌሎችን ከመቆስቆስ ይልቅ ለጋራ ጥቅምና ድል እንስራ፡፡

• ከመካከላችን ማንም እስከተጎዳ ድረስ ሁላችንም እንጎዳለን፤ ስለዚህ ለሁላችንም የምትሆን አገር በመደመር መገንባት ግድ ይለናል፡፡

• ኢትዮጵያ በሁላችንም ላብና ደም የተሰራች አገር በመሆኗ ባለቤቶቿ ሁላችንም ነን፡፡ አዲሲቷንም ኢትዮጵያ በጋራ ልንገነባ ይገባል፡፡

• ኢህአዴግ ከዳር እሰከዳር የሚሳተፉበት ድርጅት እንዲሆን መስራት ያስፈለጋል፡፡

• ኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎችን ወደ ግንባሩ ለማስገባት አቅዶ ቢንቀሳቀስም በአገራዊ ሁኔታው በጥናት እንዲመለስ የቀረበውን ጥናት ማድረስ ባመቻሉ፣ ይህን ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል ውሳኔ ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

• የተጀመረውን የፖለቲካ ምህዳር የማስፋቱ ሂደት የይስሙላ ባለመሆኑ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይገፋበታል፡፡

• የተፎካካሪዎቻችን ሀሳብ ላይሳማማን ይችላል፣ ነገር ግን የነሱን ሀሳብ በመገደብ ሳይሆን የነሱን ሀሳብ የሚያሸነፍ ሀሳብ ይዘን በመቅረብ ብቻ እንዲሆን እንሰራለን፡፡

• ዛሬ ላይ ሁነን የትላንትናውን ሁነታችንን መቀየር አንችልም፣ ይሁን እንጂ የነገዋን ኢትዮጵያ ተስማምተን መገንባት እንችላለን፡፡

• አዲስ ታሪክ ለመፃፍና ለመስራት በሚያስችል የዘመን አካፋይ አንጓ ላይ እንገኛለን፡፡

• ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ፌደራሊዝሙን ከተገበርነው ለአኛ አውድ ተመራጭነቱ አያጠያይቅም፡፡

• ሰዎች በየትኛው የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው የመስራት መብታቸው ተረጋግጦ ኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ የምትሆንበት ገፅታም ሊረጋገጥ ይገባል፡፡

• እስካሁን የብሄር ማንነት እና ኢትዮጵያዊ ማንነት ሚዛን ጠብቀው የመጡ ባለመሆናቸው የህዝብ ለህዝብ መድረኮች፣ የባህል መድረኮችና ሌሎች መድረኮችን በማዘጋጀት ከፍ ከፍ የሚያርገንን ስራ መስራት ያስፈልገናል፡፡

• መደመር ሁሉም የየራሱን ጥንካሬ ይዞ ከሆነ እምቅና አዲስ ታሪክ መፃፍ ያስችለናል፡፡

• አገራችን የገጠማት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያው ቀውስ መስኤው ከግብርገብነት ቀውስ የሚመነጭ ነው፡፡

• በሞራልና ግብረገብ የወደቀ ማህበረሰብ ውስጥ ሆነን ሰላም፣ ፍትህ፣ ብልፅግናን ማረጋገጥ ከባድ ነው፡፡

• በሞራል ልዕልና፣ በስነ ምግባር ምሳሌ በመሆን የሀይማኖት ፣ የጎሳና ማህበረሰብ መሪዎች መሪ በመሆን አርዓያነትን በማሳየት ከችግራችን እንዲንወጣ ያስፈልጋል፡፡

• ዜጎች የሚገጥማቻውን መሰረታዊ አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግር ብሎ መግለፅ አይመጥነውም፡፡

• ስራ አጥነት መቀነስ፣ የዜች የኑሮ ደረጃን ማሳደግ፣ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሰጠ ጉባኤ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ ነው፡፡
©ebc
@yenetube @mycase27