YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጲያ ውስጥ በዛሬው ዕለት በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተለቀቀው አንድ ተንቀሳቃሽ ምሥል የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰተናገዱበት ውለዋል፡፡ #በሻሸመኔ ከተማ ተፈጽሟል የተባለው ይሄው ተንቀሳቃሽ ምስል በቡድን የተሰባሰቡ ወጣቶች በዕድሜ በገፉ አዛውንቶች ላይ የድብደባ ተግባር ሲፈጽሙ ያሳያል፡፡

 DW ያነጋገራቸው የሻሸመኔ ከተማ ጸጥታና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ናዳው አምቡ #የተለቀቀው ምስል በከተማው በሚገኙ የመስኪድ መጅሊሶች መካካል #በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ #ግጭት ሳይሆን አንዳልቀረ ገልጸዋል፡፡

ድርጊቱ ከአንድ ወር በፊት የተፈጸመና ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በወቅቱ በባህላዊ ዕርቅ መጠናቀቁንም አቶ ናደው ተናግረዋል፡፡ ይሁንእንጂ ምስሉን ዛሬ የተፈጸመ አስመስለው የለቀቁት በከተማው ሰላም እንደሌለ ለማስመሰል የሚጥሩ ቡድኖች ናቸው የሚሉት ሃላፊው ከተማው በተረጋጋ  ሰላም ውስጥ እንደሚገኝ ለDW አረጋግጠዋል፡፡ የሀዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ዘገባ አድርሶናል፤

ምንጭ:- DW ~ ሸዋንግዛው ወጋየሁ
@YeneTube @Fikerassefa