በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር 05 ቀበሌ በመንበር ስላሴ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ባል
በጣለው #ቦንብ #የራሱና_የባለቤቱን ህይወት ማለፋን የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ዛሬ በ24/06/2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡10 በኮሶበር መንበረ ስላሴ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ የኮሶበር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር ሟች አለነ አገኘሁ ሲሆን የአዊ ብሄረሰብ ዞን የገቢዎች መምሪያ ምርመራ ባለሙያ የሆነችውን ከትዳር ጓደኛው ወ/ሮ አሰጋች አወቀ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በፍርድ ቤት ክርክር ላይ የቆዩ ሲሆን ሟች ወ/ሮ አሰጋች አወቀ ቤተክርስቲያን በሄደችበት ተከትሎ በመግባት በጻሎት ላይ እየለች ቦንብ በመወርወር የራሱን እና የባለቤቱን ህይወት ቀጥፏል፡፡
በተጨማሪም ቤተክርስቲያ ውስጥ በጻሎት ላይ የነበሩ 6 ግለሰቦች በቦንብ ፍንጣሪ ቀላልና ከባድ ጉዳት በመድረሱ በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኙ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ሀላፊ ዋና ኢንፔክተር አሳየ ፈረደ ተናግረዋል፡፡የሁለቱም አስክሬን ወደ ትውልድ ቦታቸው መወሰዱንም አያይዘው ገልጸዋል፡፡
Via:- እንጅባራ ኮምኒኬሽን
@YeneTube @Fikerassefa