YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
YeneTube
Photo
አብን‼️

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ለfbc እንዳረጋገጡት፥ ለአብን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ከጥር 28 2011 ዓ.ም ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) #የሀገር_አቀፍ_የፖለቲካ_ፓርቲ የምዝገባ እና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለሁለት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህጋዊ እውቅና መስጠቱንም ወይዘሪት ብርቱካን ተናግረዋል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ሰኔ 3 2010 ዓ.ም በይፋ ተቋቁሞ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል።

ምንጭ፦FBC
@YeneTube @FikerAssefa