የተለያዩ አለምአቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በፊት ገፆቻቸው አዲሲቷን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ምርጫ በተመለከተ ምን አሉ ?
ትናንት ሁለቱ ምክር ቤቶች የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የስራ መልቀቂያ ከተቀበሉ በሁዋላ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አድርገው መምረጣቸው
ይታወሳል፡፡ ይህንን መሰረት አድርገውም በርካታ የአለማችን የመገናኛ ብዙሀን በፊት ገፆቻቸው ሽፋን ሰጥተው ዘግበዋል፡፡
#ቢቢሲ የኢትዮጵያ የፓርላማ አባላት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ ሲል አስነብቧል፡፡
#አፍሪካ_ኒውስ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚዳንት አገኘች ያለ ሲሆን አምባሳደሯ በበርካታ የአለማችን ሀገሮች ታላላቅ ሀላፊነቶች ላይ የሰሩ በእውቀት የከበሩ ሰው ናቸው ብሏል፡፡
ሲ_ኤን_ኤን ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚዳንት መረጠች በማለት በፊት ገፁ አስነብቧል፡፡
#ዋሽንግተን_ፖስት ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ የለውጥ መንገድ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚዳንት ሰየመች ሲል አስነብቧል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብቸኛዋን ሴት ፕሬዚዳንት መረጠች ሲል ያስነበበው ዘቴሌግራፍ ኢትዮጵያን በሪፎርም ውስጥ እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ 20 የካቢኔ አባሎቻቸው ውስጥ ግማሾቹን ሴቶች አድርገው መምረጣቸውን አስታውሷል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተጠናቀረ
@Yenetube @Fikerassefa