YeneTube
119K subscribers
31.4K photos
484 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ኮሮና_ኢትዮጵያ

የኮሮናቫይረስ ያለበት አንድ ጃፓናዊ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት አንድ ከሦስት ቀናት በፊት ከቡርኪናፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ጃፓናዊ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ እንዳሉት ጃፓናዊ ትኩሳትና ማሳልን የመሳሰሉ የቫይረሱ ምልክቶችን የሚያሲይ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛል ብለዋል።

የጤንነቱ ሁኔታም መጥፎ የሚባል አንዳልሆነ ገልፀዋል።

ጃፓናዊው የካቲት 25 ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን ከአምስት ቀናት በኋላ የቫይረሱን ምልክት ማሳየት መጀመሩን በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል።
ከጃፓናዊው ጋር ንክኪ የነበራቸው ከ25 በላይ ሰዎች ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ጨምረው ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም ብሎም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ኢንጂነር ታከለ ኡማ በትዊተር ገፃቸው ላይ አንድ ጃፓናዊ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል ሲሉ አስታውቀው ነበር።

ከንቲባው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መውሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄ በመልዕክታቸው ላይ ጨምረው አስፍረዋል።

በቅርቡ ኢትዮጵያ የነበረና ወደ አሜሪካ የሄደ አሜሪካዊ ኮሮናቫይረስ እንደተገኘበት ተገልጾ እንደነበር ይታወቃል።

ዶ/ር ሊያ ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከየካቲት 9- የካቲት 13 2012 ዓ..ም እንደቆየና በሽታው ይዞታል ተብሎ ሆስፒታል የገባው የካቲት 30 2012 ዓ.ም እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ ከግለሰቡ ጋር ንክኪ አድርገዋል የተባሉ ሰዎች እንደመተመሩና እስካሁን ምንም እንዳልተገኘ ገልጸዋል

ከንቲባው "አንድ ጃፓናዊ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪና ከአላስፈላጊ ስብሰባዎች አንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ" በማለት ነበር መልዕክታቸውን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስፍረዋል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa