በጎንደር በጥምቀት በዓል ላይ በደረሰ የመወጣጫ መደርመስ አደጋ #ከ100_በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በጥምቀተ ባሕሩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ሲከታተሉ በነበሩ ሰዎች ላይ ለመቀመጫነት የተሠራ ርብራብ እንጨት ተደርምሶ ድንገተኛ አደጋ አድርሷል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ በተጎዱ ሰዎችና በአደጋው መንስኤ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የአደጋው መንስኤ ለመቀመጫነት የተሠራው ርብራብ እንጨት ድንገት መንሸራተቱ እንደሆነ መምሪያው አሳውቋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ደኅንነት መምሪያ ኃላፊ ተስፋ መኮንን እንዳሉት በተሠራው ርብራብ እንጨት ተቀምጠው የነበሩ ከ100 በላይ ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ለኅልፈት የተዳረጉ እንዳሉም አረጋግጠዋል፡፡ ኃላፊው የተሰማቸውን ሐዘን በመግለጽም ጉዳቱ ለደረሰባቸው ወገኖች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
አደጋው እንደደረሰም አብዛኞቹ ተጎጅዎች ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡
በሕክምና ላይ ካሉት መካከል አምስቱ ከባድ ጉዳት እንዳጋጠማቸውም ተብራርቷል፡፡ ቀላል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ሁለት የውጭ ሀገር ዜጎችና ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
መቀመጫው ከ700 እስከ 1000 ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች ያስተናግዳል ተብሎ የተሠራ ቢሆንም ፣ bባሕረ ጥምቀቱ ይካሄድ የነበረውን ሃይማኖታዊ ሥርዓትና የበዓሉን ድባብ ለማየት በጉጉት ይጠባበቁ የነበሩ በርካታ ሰዎች በእንጨቱ ላይ በመውጣታቸው ችግሩ መፈጠሩን ኃላፊው አመልክተዋል፡፡
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው ከተፈጠረው አደጋ ውጭ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳልነበርና ታቦታቱ በሠላም ወደ አድባራቱ ገብተዋል ፡፡
Via:- EBC
@YeneTube @Fikerassefa