YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአማራ ክልል መንግስት ለ4 ሺህ 280 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡⬇️

እነዚህ ታራሚዎች የህግ ታራሚዎች ከነገ ጀምሮ በይቅርታ እንደሚለቀቁ የተገለፀ ሲሆን ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥ 67 #ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡
መንግስት ያወጣውን የይቅርታ መስፈርት ያሟሉ የህግ ታራሚዎች ከነገ ጠዋት ጀምሮ ከማረሚያ ቤት እንደሚወጡ ነው የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ውቤ ወንዴ የተናገሩት፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች #ከዝቅተኛው ፍርደኛ እስከ #ዕድሜ_ልክ እስራት የተፈረደባቸው ናቸው።

በዘር ማጥፋት፣ በሙስና ወንጀል ከ10 ዓመት በላይ የተፈረደባቸው፣ ከ15 ዓመት በታች ህፃናትን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተፈረደባቸው እና በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 28 የተዘረዘሩትን የወንጀል ዓይነቶች የፈፀሙትን የህግ ታራሚዎች ይቅርታው እንደማይመለከታቸው ምክትል ኮሚሺነሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡- አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa