YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሕይወት ይቀጥላል !

ለሀገራችን ይበጃል ብለን በመረጥነው መንገድ እኔ እና ባልደረቦቼ በምንችለው ሁሉ ምርጫውን ለማሸነፍ ሌት ተቀን ደክመን ሠርተናል።

ለምርጫ የተመዘገበው ሕዝብ በካርዱ ያልተመዘገበው ደግሞ በዝምታው ምርጫውን አሳውቋል። ኢዜማ እንደ ፓርቲ ስለምርጫው ሂደት እና ውጤት ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጥ እና አቋም እንደሚይዝ ይጠበቃል።
መጪው ጊዜ የሕዝብን ምርጫ እና ውሳኔ በጸጋ ተቀብሎ ከአሸናፊው ጋር እንደ አገር ልጅ ተደጋግፎ የምንጓዝበት እንዲሆን እመኛለሁ። እስከዛሬ የሀሳብ ክርክር እና የምርጫ ፉክክር ስናደርግ ነበር። ከአሁን በኋላ ግን የተመረጠው እቅዱን ለማሳካት ያልተመረጥነው ደግሞ ለመጪው ጊዜ ለመዘጋጀት ዕድል አግኝተናል።
በምርጫ ስንወዳደር በሀገር ቤትም ሆነ ከሀገር ውጪም በሚያስፈልገን ሁሉ ለደገፋችሁን ምሥጋናችን ብዙ ነው። አሸናፊ ባያደርገንም ሃሳቦቻችንን ደግፋችሁ ድምጻችሁን የሰጣችሁን ኢትዮጵያውያንን ከልብ እናመሠግናለን። ሕይወት ግን እንደወትሮው ይቀጥላል።

#ኢትዮጵያ_እናመሰግናለን
#አዲስ_አበባ_እናመሰግናለን

አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን
@Yenetube @Fikerassefa