በኢትዮጵያ አዲስ የግል አየርመንገድ ተቋቋመ
አርብ ሰኔ 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ የግል የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ተመዝግቧል፡፡
ተቋሙ ምዝገባውን በስኬት ያጠናቀቀው አለም አቀፍ አሰራርን ተከትሎ የተቀመጠውንና በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንም የሚተገበሩትን አምስት ደረጃዎችን በስኬት አጠናቆ በመገኘቱ መሆኑም ለመረዳት ተችሏል፡፡
ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ በዛሬው ዕለት ሰኔ 3 ቀን 2014 በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተፈረመበትን ሰርትፊኬት በይፋ ተቀብሏል፡፡
በዚህም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በተካሄደው የሰርቲፊኬት ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን ተረድታችሁ፤ ተስፋ ሳትቆርጡ በትጋት በመስራት ለስኬት እንድትበቁ እመኛለሁ ሲሉ መልዕታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኤር ኤክስፕረስ አፍሪካ መስራችና ባለቤት ካፒቴይን ነስሩ ከማል በበኩላቸው፤ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ኢንስፔክተሮች ሳይሰለቹ በመስራት ለዚህ ውጤት ስላበቁን አመሰግናለሁ ሲሉ ደስታቸውን መግለፃቸውን ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ዘግቧል፡፡
ካፒቴይን ነስሩ ከማል ለረዥም ዓመታት በአውሮፕላን አብራሪነት ሙያ ላይ ተሰማርተው ሲያገለግሉ የነበሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በአሁን ሰዓት ኤር ኤክስፕረስ አፍሪካን ጨምሮ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ተመዝግበው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የአውሮፕላን አየር ትራንስፖርት ተቋማት 12 መድረሳቸውን ከባለስልጣኑ የተኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
___
#አዲስ_ማለዳ
@Yenetube @Fikerassefa