YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢትዮጵያ-ኤርትራ መንገዱ ተዘግቷል ተጨማሪ ማብራሪያ ከDW ⬇️

ኢትዮጵያና ኤርትራን በሑመራና ኦምሓጀር በኩል የሚያገናኘዉ የመኪና መንገድ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ መዘጋቱን የሑመራ ከተማ ነዋሪዎችና የአካባቢዉ ባለሥልጣናት አስታወቁ። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሰበብ #ለ20 ዓመታት ያክል ተዘግቶ የነበረዉ መንገድ የተከፈተዉ ሁለቱ ሐገራት ዓምና ባደረጉት ስምምነት መሠረት ባለፈዉ ታሕሳስ ነበር። መንገዱ ከተከፈተ ወዲሕ የሁለቱ ሐገራት ዜጎች ግንኙነት እና አነስተኛ የንግድ ልዉዉጥ እየተጠናከረ ነበር። የሴቲት ሁመራ ወረዳ የመንግስት ቃል አቀባይ #ወይዘሮ_አወጣሽ_ፀጋይ_እንዳሉት መንገዱ ዛሬ ጠዋት የተዘጋዉ በኤርትራ ድንበር በኩል ነዉ። እዚያዉ ሁመራ የሚኖሩት ነጋዴ ተስፋይ ብርሐን እንደሚሉት ግን መንገዱ #አንድ_ቀን እንደሚዘጋ ቀድም ብሎ ቢታወቅም ዛሬ ይዘጋል የሚል #ግምት ግን አልነበራቸዉም።

የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ እንደዘገበዉ የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ሥለመንገዱ መዘጋትም ሆነ ሥለተዘጋበት ምክንያት እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ በይፋ ያሉት ነገር የለም።

ባለፈዉ መስከረም ተከፍተዉ የነበሩት የዛላምበሳ-ሠርሓ፣ራማ ዓዲ ኳላ የመኪና መንገዶች አሠራርን «ሕጋዊ ለማድረግ» በሚል ሰበብ እንደተዘጉ ነዉ።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሠላም ስምምነት ካደረጉ ወዲሕ ከተከፈቱ መንገዶች እስካሁን ያልተዘጋዉ በኢትዮጵያ አፋር መስተዳድር ቡሬ በኩል ከኤርትራዉ አሰብ ጋር የሚያገናኛዉ መንገድ ብቻ ነዉ።

@YeneTube @FikerAssefa