YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ቤተ ክርስቲያን ህግ እንዲከበር ለጠየቀችው ጥያቄ "መንግስት" ምላሽ ነፈጋት !!


" አስፈላጊውን ቀኖናዊና እርምጃ ቤተክርስቲያን እንደምትወስድ " ገልፃለች !!!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ! #በአቶ_በላይ_መኮንን የተጠራው የዕወጃ መርሐ ግብር ቤተ ክርስቲያን እንደማታወቀውና ድርጊቱም ሕገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ ፤ ከቤተክርስቲያኒቱ ዕውቅናና ይሁንታ ውጭ የሚካሄደው ድርጊት "መንግሥት" እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመግለጫ ጠይቃ ነበር።

ይሁን እንጂ ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫና ማሳሰቢያ እንዲሁም ውግዘት ወደጎን በመተው #አቶ_በላይ_መኮንን በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጠ ሲሆን ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕገ-ወጥ ነው ያለችው ድርጊት "መንግሥት" እንዲያስቆም ብትጠይቅም በ"መንግሥት" በኩል ምላሽ ተነፍጎታል።

ቋሚ ሲኖዶሱ ከ2 ቀናት በፊት ፤ ከመዋቅር አፈንግጠው በወጡ ፓለቲከኞች የተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ቤተክርስቲያን የማታውቀውና ሕገ ወጥ የሆነ ፣ ቤተክርስቲያንን ከስሯ ለመናድ የሚደረግ እንደሆነ በመግለጽ ፤ ሕዝበ ክርስቲያን በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ቤተክርስቲያኒቱ ያሳሰበች ሲሆን ፤ "መንግስት" ሕገ-ወጥ ድርጊቱን እንዲያስቆም በመጠየቅ ይህ የማይሆን ከሆነ አስፈላጊውን ቀኖናዊና እርምጃ ቤተክርስቲያን እንደምትወስድ መግለጿ የሚታወቅ ነው።


ምንጭ:- mereja.com
@YeneTube @FikerAssefa