YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ማስታወሻ 📌ነገ ነሃሴ 8፣ 2010 3 ሰአት ላይ የ#አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄን ወደ ሀገር ውስጥ የመግባትን መርሃ ግብር በተመለከተ፤ የሀገር ወስጥ አዘጋጅ ኮሚቴ የአቀባበሉን ስነስርአት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ሆቴል ይሰጣል!!

@YeneTube @Fikerassefa
#አርበኞች_ግንቦት_7 ዛሬ ነሀሴ 27/12/10 ዓ.ም 📌አሁን ጎንደር ከተማ ሲገባ ደማቅ የጀግና አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል።

📌የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች ወታደራዊ ካምፑን በመዝጋት ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጀመሩት ትናንት ነው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
UPDATE መረጃ #አርበኞች ግንቦት ሰባት ⤵️

የአግ7 አመራሮችንና አባሎችን የያዙት አውሮፕላኖች ነገ ጠዋት 12:15 አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳሉ።

©Nati
@YeneTube @Fikerassefa
#አርበኞች ግንቦት 7

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ የሁሉም ሀሳብ አራማጆች #ለዘለቄታዊ ለውጥ ቁጭ ብሎ መወያየት እንደሚገባ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

ሊቀመንበሩ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ #የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ለመጠበቅ ከመጣር ይልቅ #ትክክለኛ ምርጫ ማካሄድ የሚችል ስርዓትና #ተቋማት መኖራቸውን ማረጋገጥ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ገልፀዋል።

የለውጡ ኃይል የሀገሪቱን ረጅም የመከራ ቀን በመሳጠርም ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉንም አስታውቀዋል።

ከሁሉ በላይ ሁላችንም ለሀገር ለውጥ #እንወያይ የሚል ሀሳብ አንግቦ ለተግባራዊነቱም መስራቱ መጪው ጊዜ #ብሩህ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳሰነቃቸውም ገልፀዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከሁሉም ኃይሎች ጋር ተመካክሮ የተገኘውን ይህን እድል መጠቀም እንደሚሻም ነው ያሰትወቁት ።

በፖለቲካ ምክንያት ሰውን እንደጥላት የማየት አስተሳሰብ ከህብረተሰቡ ሊወጣ ይገባል #መረጋጋት ያስፈልጋል ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

የሀገሪቱን ዘለቂ ሰላም ለማምጣትና ዲሞክራሲያዊ ባህልን ለማጎልበት ህብረተሰቡ ለመወያየትና ለመደማመጥ የሚቻልበት ሁኔታ መፍጠር አለበት ስለዚህም ለሁሉም ነገር ነገሮችን #ተረጋግቶ ማሰብ ይገባል ብለዋል።

እኛ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ ከማድርግ ውጪ ሌላ ዓለማ የለም ይህን ስራ ለመተግበር ግን ብዙ ስራ ይጠይቃል ይህንንም ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ ነን ብለዋል ሊቀመንበሩ በመግለጫቸው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እኛ በህብረ ብሔራዊ ስሜት ሀገርን ለመገባት አስበን ብንመጣም #በብሔር ከተደራጁ አካት ጋርም ቢሆን በዲሞክራሲያዊ መልኩ ለመወያየት ዝግጁ ነን ብለዋል።

©etv
@yenetube @mycase27