YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አማርኛ የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ዶ/ር አብይ ጠየቀ።

እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ #አማርኛ ከእንግሊዘኛ ፣ ከፈረንሳይኛ እና ከአረብኛ ጋራ የአፍሪካ ህብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን ጥያቄ አቅርቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
#አማርኛ#ቲክቶክ "ቁጥጥር ስርዓትን" እና "የጥላቻ ንግግር መለያን” ለማለፍ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን ጥናት አረጋገጥ

#ኢትዮጵያ እና በዳያስፖራው ማህበረሰብ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተናጋሪዎች ያለው አማርኛ በቲክቶክ ማህበራዊ ሚዲያ "የይዘት ቁጥጥር ስርዓትን" እና "የጥላቻ ንግግር መለያን” ለማለፍ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ስትራቴጂክ ዲያሎግ ኢንስትቲዩት የተሰኘ ተቋም ባደረገው ጥናት ተመላከተ።

የሴሚቲክ ቋንቋ የሆነው አማርኛ ለዚህ ተግባር ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው በቲክቶክን የይዘት ቁጥጥር ስርዓት ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በመጠቀም  መሆኑ ጥናቱ አመላክቷል።

ጥናቱ አማርኛን በሁለት የተለያየ መንገድ በመጠቀም የተጻፉ 134 አስተያየቶችን ለይቷል። የመጀመሪያው ዘዴ "ኮድድ” የተሰኘ ሲሆን ይህም "የግዕዝ ፊደላትን ተጠቅሞ የጥላቻ ንግግርን በቀጥታ ወደ አማርኛ መተርጎም" ይጨምራል። ሁለተኛው ስልት ደግሞ “ባይፓስ” የተባለ ሲሆን  "በአውሮፓ ቋንቋ  የተጻፉ የጥላቻ ንግግርን ከአማርኛ ጽሁፍ ጎን ማስቀመጥ" ነው።

ሪፖርቱ እንደገለጸው፤ "በቲክቶክ እንዲጠፉ ሪፖርት ከተደረጉ 16 አስተያየቶች ውስጥ መድረኩ 5 አስተየቶችን ብቻ አጥፍቷል ወይም የመታየት እድላቸውን ገድቧል። "ይህ የሚያሳየው የየቲክቶክ ሲስተም በእንግሊዘኛ የተጻፉ እና ሪፖርት የተደረጉ፣ ከአማርኛ ቋንቋ ጽሑፍ ጎን የሚታይ እንኳ ቢሆን የጥላቻ ንግግርን መለየት እንደማይችል ነው” ሲል ጥናቱ አክሏል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍274👎1