YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
⬆️
በሶሻል ሚዲያ የሚናፈሰው የቴዲ አፍሮ የአዲስ አመት ኮንሰርት #አልተከለከለም ⬇️

የአርቲስቱ የአዲስ አመት ኮንሰርት በመንግስት እንደተሰረዘ በብዛት ሲፃፍ አየሁና የከተማውን አስተዳደር እና ለአርቲስቱ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን ለማናገር ሞክሬ ነበር። እንደወረደ እንዲህ ላቅርበው:

የአ/አበባ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ፕረስ ሰክረታሪ ፌቨን ተሾመ:
"በፍፁም አልተከለከለም! የሆነው እንዲህ ነው: የቴዲ አፍሮ ፕሮሞተር እና ማናጀሩ መስቀል አደባባይ ኮንሰርት እንዲያቀርቡ ጠየቁን። እኛም ይህንን ለፀጥታ አካላት ስናሳውቅ እነሱ ግን ለምን ግዮን፣ ስታዲየም ወይም ሌላ ቦታ አይሆንም ብለው አስተያየት ሰጡ። ም/ከንቲባው ግን እዛው መስቀል አደባባይ ይሁን፣ ባይሆን አካባቢውን ለፀጥታ ሲባል ማጠር ይቻላል የሚል መልእክት አስተላለፉ። በዚህም መሰረት የፈቃድ ደብዳቤውን ልከናል። ስለዚህ ሙሉ ፈቃድ በከተማው አስተዳደር ተሰጥቷል። አሁን ግን ቴዲ ተከለከለ የሚል ነገር ሰማን።"

በኮንሰርት ዝግጅቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆነ ግለሰብ:
"ስሜን አትጥቀሰው ግን ይህን መረጃ ልስጥህ። አልተከለከልንም። የፈቃድ ደብዳቤውም እጄ ላይ አለ። ኮንሰርቱ ወደፊት ይካሄዳል። ያሰብነው ለአዲስ አመት ነበር ነገር ግን በራሳችን ጉዳይ አልተሳካልንም። በምንፈልገው ደረጃ ሳውንድ ሲስተም ሀገር ውስጥ ሊገኝ አልቻለም። ሀገር ውስጥ ያለው የዋፋ ድርጅት ነበር እርሱ ደግሞ ቀድሞ ተይዟል። ይህ ነገር in advance አራት እና አምስት ወር የሚፈልግ ነገር ነው። ስለዚህ ለዛ አሁን እየተዘጋጀን ነው። የከተማ አስተዳደሩ በፈለግን ግዜ ፍቃድ መጠየቅ እንደምንችል ነግሮናል። ከእነሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነው ያለን።"

Via:- Elias meseret
@YeneTube @FikerAssefa