YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ታንዛንያ አትክልቶችን ወደ አውሮፓ አገራት ለመላክ የኢትዮጵያን አየር መንገድን እንደምትጠቀም አስታወቀች፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ በርካታ አየር መንገዶች መብረር ያቆሙ በመሆኑ የታንዛኒያ መንግስት ወደ አውሮፓ የሚልካቸውን ምርቶች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል አገልግሎት መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡

የታንዛንያ መንግስት የአትክልት ምርቶችን ለአውሮፓ ገበያ ለማቅረብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚጠቀምበት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በካርጎ አገልግሎት ለአውሮፓ ገበያ ጭነቶችን በማቅረብ ረገድ ጥሩ አፈጻጸም እንዳለው የታንዛንያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጃክሊን ሚኪንዲ ዘጋርዲያን ለተሰኘው የአገሪቱ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ሚኪንዲ እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር ካርጎ አውሮፕላን ረቡዕ እና እሁድ የሀገሪቱን የአትክልት ምርት ከኪሊማንጃሮ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በመነሳት ወደ አውሮፓ ከተሞች ይበራል ተብሏል፡፡

የካርጎው አውሮፕላኑ 30 ሜትሪክ ቶን አትክልት የመጫን አቅም ያለው ሲሆን ቤልጄምን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን ከተሞች ጭነቶችን እንደሚያጓጉዝ ተደራሽ ያደርጋል ብለዋል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa