YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ታመናል

#አቡሽ_ዘለቀ

ይቅርታ ፕሮፌሰር አንድ ጥያቄ ነበረኝ
ዌል መጀመሪያ ሂድና በዘርህ ተደራጅተህ ና
ታመናል ታመናል ታመናል በጣም ...
ሃያ ሰላሳ አመት ፊደል ቆጥረን አውቀን
የተሻለ ሃሳብ እንዴት ማምጣት አቃተን
ዛሬም የዘር ሃረግ ገመድ የሚጠልፈን
ሁሉም የየራሱን ገንብቶ ካጠረ
ሁሉም የየራሱን ዘር ከመለመለ
የአብሮነትን ካባ ማን ሊያለብሰን መልሶ
ለሩብ ክ/ዘመን የበረደን መች አንሶ
ከየትኛው ክልል ነው ከየትኛው ከተማ
ከዚያኛው ሰፈር ነው ከዛ ጎሳ መጣ
መቼ ነው የሚለቀን እናስተውል ለአንድ አፍታ
ይበቃል እንራቀው ይህን ክፉ በሽታ

ታመናል
እርምእርም ርምርም ስንት ሺህ አመት ልኖር
እርምእርም ርምርም ከህሊናዬ ርቄ
እርምእርም ርምርም በቀል ተንኮል ክፋት ለትውልድ አውርሼ
እርምእርም ርምርም ከጎዳናው ልውደቅ ልለምን አንጥፌ
እርምእርም ርምርም ሆዴን ከምሞላው ሰው ከሰው አራርቄ
ሃያ ሰላሳ አመት ፊደል ቆጥረን አውቀን
የተሻለ ሃሳብ እንዴት ማምጣት አቃተን
ዛሬም የዘር ሃረግ ገመድ የሚጠልፈን
ምክንያት እየፈለግን ሰበብ እየፈጠርን
በትንሽ ትልቁ ጦር እየተማዘዝን
አይደለም የሚበጀን
አይደለም የሚጠቅመን

በቀን ሶስቴ እንኳን መብላት እያቃተን
የማን ዘር ነው ከእሳት ከመብረቅ የተሰራ
የማን ዘር ነው ከጭድ ከሰበዝ የተሰራ
አንዱን እያሳነስክ አንዱን አታግዝፈው
ሆዱ አምላክ አትሁን ፍቅር ስበክ አንተ ሰው
እርምእርም ርምርም የት ነው የተማሩት
እርምእርም ርምርም እነኛ የአድዋ ጀግኖች
እርምእርም ርምርም የት ነው የተማሩት
እርምእርም ርምርም እነኛ የአድዋ አርበኞች
እርምእርም ርምርም ከራሳቸው አልፈው
እርምእርም ርምርም ምሳሌ የሆኑት ለአለም
እርምእርም ርምርም ለሰው እንጂ ለፀብ ስለታደሉ አይደለም

...ጌጡ ተመስገን እንደፃፈው....
@YeneTube @Fikerassefa