YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#update ​በአሶሳ በግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ አራት ሰዎች #ተያዙ

የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ትናንት በአንድ ሰው ግድያ የጠረጠራቸውን አራት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ፡፡

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር #አኑር ሙስጠፋ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በከተማው አንድ ሆቴል በሁለገብ ጥገናሥራ በተሰማራ ወጣት ህልፈት ጋር በተያያዘ ወንጀል ነው፡፡

ግድያው የተፈጸመው በግለሰቦች መካከል በተከሰተ #ግጭት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተደረገው ምርመራ ሂደት በአብዛኛው ተጠናቆ መዝገቡ #ለዐቃቤ ሕግ መተላለፉን ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡

የከተማውን ጸጥታ ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመመለስ በከንቲባው የሚመራ ኮማንድ #ፖስት ተቋቁሞ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ፦ ኢዜአ
@yenetube @mycase27