YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሐረር ከተማ ታማለች ⤵️

ሐረር ከተማ ላለፉት ስድስት ወራት #ውሃ ተጠምታለች፣ በቆሻሻም ታፍናለች - የዚህ ምክንያቱ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች #በ5 ቀን ውስጥ #10 #ሚሊየን ብር እንዲከፈላቸው በመጠየቅ የውሃ መስመሩን በመስበራቸውና ቆሻሻም አናስደፋም በማለታቸው ነውሀ

እስካሁን ድረስ ከምሰራቅ ኦሮሚያ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ቄሮዎች ጋር ምክክር ቢደረግም መፍትሄ አልተገኘም…ወጣቶቹ ከውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ሰራተኛው ቁልፉን ነጥቀው ወስደዋል፣ ሞተሮቹን አጥፍተዋል፣ የውሃ መስመሩንም ሰብረው ውሃው በከንቱ እየፈሰሰ ነው፡፡

©ሸገር FM
@YeneTube @Fikerassefa