YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በዩኔስኮ የተመዘገቡት የ #ኮንሶ አምባ መንደሮች ቅርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

በዩኔስኮ የተመዘገቡት የኮንሶ አምባ መንደሮች ቀርስነታቸውን የመልቀቅ አደጋ እንደተጋረጠባቸው የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገለጸ።

የኮንሶ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ሰራዊት ዲባባ እንደገለጹት፤ ዩኔስኮ 12 የኮንሶ አምባ መንደሮችንና የማህበረሰቡ የአኗኗር ዘይቤን ዓለም አቀፍ ቅርስ አድርጎ መዝግቧል::

በእነዚህ አምባ መንደሮች ባህላዊ ቤቶች፣ ባህላዊ መሰብሰቢያ ስፍራዎች፣ የትውልድ መቁጠሪያ ትክል እንጨቶች፣ የጀግንነት መዘከሪያ ሀውልቶች እንዲሁም ሌሎች የኮንሶን ህዝብ እሴትን የሚያሳዩ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ቅርሶች እየተጠበቁ ለትውልድ እንዲሸጋገሩ እየተሰራ የቆየ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት ግን በአምባ መንደሮቹ ጎጆ ቤቶችን ቆርቆሮ በማልበስ ቅርስነቱን እንዲለቅ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቅርሱ ይዘት ላይ የተጋረጠው አደጋ ከፍተኛ መሆኑን የሚገልጹት ኃላፊው፤ በአሁኑ ሰአትም ከመንደሮቹ ካሉት ቤቶች 50 በመቶ የሚሆኑት ቅርስነታቸውን በሚለቅ መልኩ ቆርቆሮ መልበሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ምክንያቱ ስለ ቅርሱ ያለው የግናዛቤ ክፍተት እንዲሁም በአካባቢው የሳር አቅርቦት አለመኖር ሲሆን፤ ይህንን ችግር ለመፍታትም ግንዛቤ የመፍጠርና በክልሉ እንዲሁም በፌደራል መንግስት የሚተዳደሩ ፓርኮች ሳሮችን የሚያቀርቡበት አሰራር መፍጠር ላይ እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው፤ ቅርሱን ለመጠበቅ በሚደረገው ጥረት ነዋሪዎች የሚያነሱት አንዱ ጥያቄ የሳር ክዳን መወደድ በመሆኑ ይህንን ለመቅረፍ ክልሉ በሚያስተዳድረው ማዜ ብሄራዊ ፓርክ በተወሰነ ቦታ ላይ ሳር ለማልማት ፕሮጀክት እየተነደፈ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
@Yenetube
👍17😭73