YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በአማራ ክልል በመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚሰሩ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ)
አባላት #በብልፅግና_ፓርቲ ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ ስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

አባላቱ በብልፅግና ፓርቲ አስፈላጊነት ፣ ፕሮግራም ፣ ህገ ደንብ ዙሪያ ነው ከስራ ሃላፊዎቹ ጋር እየመከሩ የሚገኙት፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አጥነትን እና የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ ፣ ሀገራዊ መግባባትን ከመፍጠር አኳያ እንዲሁም የፓርቲው ህገ ደንብ ከኢህአዴግ ህገ ደንብ የሚለይበት ነጥቦች ምንድ ናቸው የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ለጥያቄዎቹም አማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው እና ሌሎች የፓርቲው የስራ ሃላፊዎች ምላሽ እየሰጡበት ይገኛል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
👍1