YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በምዕራብ_ጎንደር ዞን ቋራ እና #በባሕር _ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ኢንስቲትዩቱ አስታወቀ

#አማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ እና በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ በርካታ ሰዎች እየተያዙ መሆኑን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አሰጣጥ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ እንደገለጹት ወረርሽኙ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ የሚደርሰው የበሽተኛ ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በቀን ውስጥ በርካታ ሰዎች በበሽታው እየተጠቁ ነው ብለዋል።

አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በማስከተል ለሞት የሚዳርገው በሽታው በክልሉ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ መከሰቱን አስረድተዋል ሲል አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ሲስተር ሰፊ ደርብ የኮሌራ የተበከለ ውኃ እና ምግብን በመጠቀም የሚከሰት ሲኾን ሰዎች በብዛት በሚሠባሠቡባቸው ቦታዎች በተለይም ንጹህ የመጠጥ ውኃ እና ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ በሌለበት አካባቢ በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በሽታውን ለመከላከል ከበሽተኛ ጋር ንክኪ ከተደረገ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ውኃን በኬሚካል አክሞ እና አፍልቶ መጠቀም እንዲሁም የበሽታው ምልክቶች ከታዩ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያስፈልጋል ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍83😭3😁1