ሰልፍ‼️ ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ሰልፍ አለመኖሩን አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን አስታውቋል‼️
አንዳንድ ግለሰቦች #ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ #ሰልፍ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ፖሊስ #ገለፀ፡፡ ሰልፉ በከተማው አስተዳደር ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ #እውቅና የሌለው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ስፍራዎች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እንዲሁም የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ታህሳስ 6 እና እሁድ ታህሳስ 7/2011 ዓ/ም አንዳንድ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩም ይሁን በፖሊስ እውቅና የሌለው መሆኑን የኮሚሽኑ ኢንዶክተሪኔሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ከላከው ዜና መረዳት ተችሏል፡፡
ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ #ህገ_መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን #አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሞ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑ መልእክቱን አስተላፏል፡፡
በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡
ምንጭ:- አዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሺን
@YeneTube @Fikerassefa

ሰበር ዜና ‼️
ታከለ ኡማና እስክንድር ነጋ ተገናኙ
❇️ህዝባዊ ስብሰባዎች እንዲፈቀዱ ተስማሙ❇️
በዛሬው ዕለት፣ መጋቢት 30/ ቀን 2011 ዓ.ም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማና የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት፣ እንደመነሻ ሃሳብ ሆኖ፣ በአዲስ አበባ ጉዳይ ልዩነቶች እንዳሉ፣ ልዩነቶች ግን በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለባቸው ተስማምተዋል፡፡
በቀጣይነትም፣ ወደዋነው አጀንዳ ለመግባት፣ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በባልደራስ አዳራሽ የተሰበሰቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ያወጡትን የአቋም መግለጫ በፅሁፍ እንዲቀበሉ በእስክንድር በኩል ጥያቄ የቀረበ ሲሆን፣ አቶ ታከለ ጥያቄውን ለመቀበል ፈቃደኛ #አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ እስክንድርም ለአቶ ታከለ በሰጠው ምላሽ፣ የህዝቡን #ጥያቄ እንዳልተቀበሉ ለህዝብ #ይፋ_እንደሚደረግ ገልፆላቸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ጉዳይ ያሉትን ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዲያስችል፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሊፈቀዱ እንደሚገባ በእስክንድር በኩል ሃሳብ ቀርቦ፤ አቶ ታከለ ኡማ ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ ተቀብለው ከከተማዋ #የፀጥታ ኃላፊ #ጋር_በስልክ_አገናኝተውታል፡፡ በዚህ መልክ ህዝባዊ ስብሰባዎች ያለምንም ችግር እንዲደረጉ ከከተማዋ ባለስልጣናት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በዚህም መሰረት፣ ከሚቀጥለው #ቅዳሜና_እሁድ_ጀምሮ፣ በየክፍለ ከተሞች በሚጠሩ ህዝባዊ ስብሳባዎች በኩል የአደረጃጀት ስራ የሚጀምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት (ባልደራስ)
አዲስ አበባ
መጋቢት 30/2011 ዓ.ም
@YeneTube @FikerAssefa