#ጥናት
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው፣ በዕጣ የቤት ባለቤት የሆኑ ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት (ACRC) እና ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) በጋራ ባደረጉት ጥናት ማረጋገጥ መቻላቸውን አስታውቀዋል።
ሁለቱ ተቋማት ጥናቱን ለአንድ ዓመት ያህል ነው ያደረጉት።
በጥናቱ ከ6 በላይ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊ ሽግግርና በወጣቶች አቅም ግንባታና በመኖሪያ ቤቶች ላይ የተደረገ ነው።
ጥናቱ ምን ይላል ?
- በአዲስ አበባ ከተማ ከመነሻውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም፡፡
- መንግሥት 40/60 ወይም የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ለደረሳቸው ሲያቀርብ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ስለማይገነቡ፣ ዕድለኞች መልሰው አፍርሶ ለመሥራት ይገደዳሉ ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።
- የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ፦
* ለኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ፣
* የሲራሚክ ንጣፍ፣
* ለመፀዳጃ ቤት መስመር፣
* ግድግዳ እንደገና ለመሥራትና ሌሎች የጎደሉ ነገሮች ለማሟላት ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።
- እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ መንግሥት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብዓት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድረስ ጥራታቸውን በመጠበቅ ማቅረብ ይኖርበታል።
በተጨማሪ ...
☑ በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ተስማሚ የሆኑ ነገሮች እንደሌላቸው ታይቷል። ወጣቶች በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ፣ በኢመደበኛ ዘርፍና በጤና ላይ ያላቸውን በጎ ተግባራትና ያሉባቸው ችግሮች ተለይተው በጥናቱ ተካተዋል።
☑ በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አብዛኛውን የቤት አቅርቦት ተፈጻሚ የሚሆነው በመንግሥት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ቤት አልሚ ድርጅቶች ተቋቁመው የማኅበረሰቡን የቤት ጥያቄ እየመለሱ መሆናቸው የሚበረታታ ነው።
☑ በቤት አቅርቦት ላይ ለውጦች እየመጡ ቢሆንም አሁንም የመሬት አቅርቦት፣ እንዲሁም በዝቅተኛና በመካከለኛ ገቢ ላይ የሚገኙ ሰዎች ቤት ለመሥራት ቢፈልጉ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ነው።
👉 በአጠቃላይ ጥናት የተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታትና በጥናቱ የቀረቡ ግኝቶች መሬት ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የሚቀርቡ ይቀርባሉ ተብሏል።
#ሪፖርተር_ጋዜጣ

👍55❤10😁6👎5
በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች በሚያስመዘግቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚፈቅደው መመሪያ ቅሬታ ቀረበበት፡፡
መመሪያው ግልፅ እና ያልተብራራ ነው ሲል የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማኅበር ቅሬታውን አሰምቷል፡፡
የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ፣ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ገቢራዊ የሆነው የቅድመ-ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና አወጣጥ በትክክለኛ መንገድ ግምገማ ሳይደረግበት ዕርምጃ የሚያስወስድ መመሪያ ማውጣት አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡
በተለይ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱ ምን ይመስላል የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ሳይፈተሽ ወደ ዕርምጃ መገባቱ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከማቀጨጭና ከዘርፉ ከማስወጣት የዘለለ ምንም ዓይነት ሚና እንደማይኖረው ዋና ሥራ አስኪያጁ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
መመሪያው የተብራራ ስላልሆነ በድጋሚ እንዲታይ ማኅበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡
መመሪያውን በተመለከተም ሆነ ለሌሎች ጥያቄዎች ማኅበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን ዋና ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡
"በተከታታይ ሦስት ጊዜ በመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ ዕርምጃ ይወሰዳል" የሚለው በተቋም ደረጃ ነው ወይስ በፕሮግራም (በዲፓርትመንት) ያስመዘገቡ ናቸው ለሚለው ጥያቄ መመሪያው ውስጥ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
"የከፍተኛ ትምህርት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ" የሚል ስያሜ የተሰጠው መመሪያው፣ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈቃድ እንዲታደስለት ትምህርት ካጠናቀቁት ውስጥ የወቅቱ ተመራቂዎች ቢያንስ 25 በመቶ የሚሆኑት የመውጫ ምዘናን ፈተና ማሳለፍ ይኖርባቸዋል ይላል፡፡
በኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቅበላ በተደረገላቸው ተማሪዎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን በመመሪያው ተካቷል፡፡ #ሪፖርተር
@tikvahuniversity

👍34❤5👎3