YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ የተፈጠረውን ችግር በቶሎ አጣርቶ ለማሳወቅ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ችግሩ በማን እና እንዴት እንደተፈጠረ በማጣራት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡የመጀመሪያዎቹ ማለትም ሰኔ 6 እና 7 የተሰጡት ፈተናዎችት ችግር እንደሌለባቸው፣ የሰኔ 10 እና 12 ደግሞ የመጨመር ባህርያ እንደታየባቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቆ ነበር፡፡ የተወሰነ ቦታ ላይ ደግሞ ከሚጠበቀው በላይ ግሽበት አሳይቷል ነበር ያሉት ዳይሬክተሩ አቶ አርዓያ ገብረ እግዚአብሔር፡፡በመሆኑም የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት የተሰጡት ፈተናዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያን እነዲወስኑ መመረጣቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

ይህም ተማሪዎችን በፍትሃዊነት እንደሚያወዳድር እና ከችሎታቸው ውጭ ተማሪዎችን እንደማያበላልጥ ነው የተገለጸው፡፡የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥቡ ስንት ይሆናል? የሚለው ወደፊት እንደሚገለጽም ነው የተነገረው፡፡ #ችግሩ_በማን_እና_እንዴት_ተፈጠረ? #ማንስ_ኃላፊነቱን_ይወስዳል? የሚለውን የሚያጣራ #ለጠቅላይ_ _ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆነ ኮሚቴ እንደተቋቋመ ታውቋል፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ጌታሁን ጋረደው (ዶክተር) ጥፋቱ መሠረታዊ እና ከፍተኛ በመሆኑ ጉዳዩ በአስቸኳይ ተጣርቶ ይፋ እንደሞሆን ነው የገለጹት፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ መሠረት የእንግሊዝኛ፣ አፕቲቲውድ፣ ሂሳብ፣ ጂኦግራፊ እና ፊዚክስ ውጤቶች የተማሪዎቹን መግቢያ ይወስናሉ።ይህ ውሳኔ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ጉዳዩ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ችግሩ እነዴትና በማን ተፈጠረ? በሌሎች የትምህርት አይነቶች በራሳቸው ሰርተው የተሻለ ውጤት ላመጡ ተማሪዎችስ ችግር አይፈጥርም ወይ? የሚሉና ሌሎችም ግልጽ መሆን ያባቸው ጥያቄዎች አሁንም ምላሽ ይሻሉ፡፡

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa