YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አፕል የአይፎን ስልክ የመሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ ሊያደርግ መሆኑን ፍንጭ ሰጠ

የአፕል ኩባንያ ሀላፊ ቲም ኩክ በተወሰኑ ስፍራዎች የአይ ፎን ስልኮች የመሸጫ ዋጋ ላይ #ቅናሽ ሊደረግ ይችላል በማለት #ፍንጭ መስጠታቸው ተነግሯል።

አፕል የዋጋ ማስተካከያውን የሚያደርገው እያጋጠመው ያለውን የሽያጭ #ማሽቆልቆል ለማስተካከል እንደሆነም ነው የተገለፀው።

ኩባንያው የገቢው መቀነስን ከቻይና ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ጋር ያያያዘ ቢሆንም፥ የኩባንያው ሀላፊ ቲም ኩክ ግን ከዚህ የተለየ ሀሳብ አላቸው።

እንደ ሀላፊው ቲም ኩክ ገለጻ፥ የአፕል ገቢ እንዲቀንስ ካደረጉ ነገሮች መካከል የዋጋው መወደድ አንዱ ነው።

በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ያለው የዶላር የውጭ ምንዛሬ ዋጋ የአይፎን ስልኮች ውድ አንዲሆን ማድረጉንም አንስተዋል።

የአፕል ኩባንያ በያዝነው ወር የአይፎን ስልኮችን የመሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረግ መጀመሩን የገለጹት ቱም ኩክ፥ የዋጋ ማስተካከያው በተለይም ከውጭ ምንዛሬ ጋር ተያይዞ የአይፎን ስልክ መግዛት የሚከብዳቸውን ደንበኞች ማእከል ያደረገ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa