ትውልዱ ብሔርን መሰረት አድርጎ #መፈራረጅና_መጠላላትን እንዳይወርስ መጠንቀቅ እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ ኢብራሂም አሳሰቡ።
አፈ ጉባዔዋ ይህን ያሉት ዛሬ በምስራቅ ኢትዮጵያ ያሉ ክልሎች የተሳተፉበት #በድሬደዋ እየተካሄደ ባለ የሰላም ኮንፍረንስ ላይ ነው።
ለሁለት ቀናት ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በኮንፍረንሱ #መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉትም በአገሪቷ ”የእከሌ ብሔር ካንተ በላይ ተጠቃሚ ሆኗል፣ የእከሌ ብሔር የበላይ ሊሆንብህ ነው” የሚሉ ጥላቻ ሰባኪና ጥርጣሬን የሚዘሩ ቃላት ሥር እየሰደዱ ነው።
በዚህ ምክንያትም በብሔር መፈራረጅና ጥላቻ እየሰፋ መጥተዋል ብለዋል።
በዚህም ምክንያት በርካቶች በአሰቃቂ መንገድ እየተገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ፣ ለፍተው ያካበቱትን ጥሪት እያጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ ኢዜአ
@yenetube @mycase27