YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#​በሻሸመኔ ከተማ ሰው በመግደልና ዘቅዝቆ በመስቀል ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ #ሊመሰረትባቸው ነው

በሻሸመኔ ከተማ ሰው በመግደልና ዘቅዝቆ በመስቀል ወንጀል #የተጠረጠሩ 14 ግለሰቦች በቁጥጥር ስል አውሎ በስድስቱ ላይ ክስ እንደሚመሰርት የከተማው ፓሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ ነሃሴ 6 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሀመድ አቀባበል ስነ ስርዓት ላይ ግርግር በመፍጠር አንድ ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ በመስቀል ወንጀል ጠርጠራቸውን የአቃቤ ህግ መዝገብ ይጠቁማል።

የከተማው ፓሊስ መምሪያ አዛዝ ኮማንደር #መኮንን ታደሰ ለጣቢያችን እንዳሉት፥ ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል በስድስቱ ላይ አቃቤ ህግ ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ በማግኘቱ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት እንደሚቀርቡም አስታውቋል።

ነሃሴ 6 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት8 በተፈጠረው ግርግርና ግፊያ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የከተማው ፓሊስ ተሽከርካሪ ቃጠሎ እንደደረሰበት ይታወሳል።
©FBC
@yenetube @mycase27