YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዛሬው ዕለት በአዊ ዞን በፋግታ ለኮማ ወረዳ ልዩ ስሙ #ሉሊስታ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አዳጋ የ18 ሰዎች ህይወት #ጠፋ

በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የትራፊክ ባለሙያ ሳጅን መልካሙ ልየው እንደገለፁት፥ አደጋው የተከሰተው #የመከላከያ ኦራል ኮድ ቁጥር መከ-01335 እና የህዝብ #ማመላለሻ አይሩፍ ኮድ 3 አማ 20705 የሆነ መኪና በፈጠሩት #ግጭት መሆኑን ተናግረዋል።

በአደጋው እስካሁን የ18 ሰዎች ህይዎት ማለፉ #መረጋገጡን እና በሌሎች ሰዎች ላይም ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል።

የአደጋው መንስኤም እየተጣራ መሆኑን ሳጅን #መልካሙ ተናግረዋል።
©FBC
@yenetube @mycase27