YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በወቅታዊ ሀገራዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ #ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዋናነት የቀረበላቸው ጥያቄ በሀገሪቱ ካለው የህግ የበላይነትን ከማስከበር ጋር መንግስት እየወሰዳቸው ያላቸውን እርምጃዎች በተመለከተ የተያያዘው አንዱ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸውም ከዚህ በፊት መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚወስዳቸው ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ከሰብዓዊ መብት አንፃር ጥያቄ የሚያስነሱ እንደነበር አስታውሰዋል።

መንግስት ይህን ከሰብዓዊ መብት ጥሰት አንፃር ተገቢ ያልነበሩ እርምጃዎችን ሲወስድ ህግ አስከበረ ሲባል መቆየቱንም በማንሳት።

አሁን ግን ያዓይነት አሰራር ትክክል እንዳልሆነ በመረዳት በለውጡ ውስጥ ማሻሻያዎች እየተደረጉ በመሆኑ ህግን በተከተለ መልኩ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልፀዋል።
በሶማሌ ክልል፣ በቡራዩ፣ በጌዴኦ፣ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግጭት በመፍጠር እና ለሰው ህይወት እና ለንብረት መጥፋት ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች ለፍርድ መቅረባቸውን በመጥቀስ ይህ የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ ነው ብለዋል።

ህግን ተከትሎ የህግ የበላይነትን በማስከበሩ ስራ ያሉ ከፍተቶች ቢኖሩም በዚያው አግባብ የሚታዩም ይሆናል ብለዋል።

Via - FBC-በሰላማዊት ካሳ
@YeneTube @FikerAssefa