#update ቤኒሻንጉል ክልል ⤵️⤵️
#ከቤኒሻንጉል ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል እርዳታ የጫኑ 9 መኪኖች በጸጥታ ችግር #ምክንያት ወደ ካማሺ ዞን መንቀሳቅስ አልቻሉም ተባለ።
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአሶሳ ከተማ ቆመው የሚገኙት እኒህ መኪኖች 2, 358 ኩንታል ስንዴ፣ በቆሎና የተለያዩ አልሚ ምግቦችን የጫኑ #ናቸው።
የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከቤኒሻንጉል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮና ከመከላከያ ጋር በመተባበር መኪኖቹን ወደ ቦታው ለማንቀሳቀስና ወደ ተፈናቃዮቹ ለማድረስ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።
በተያያዝ ዜናም የቤኒሻንጉሉን ግጭት የሚያጣራው ኮሚሽንም በመንገድ መዘጋት ምክንያት ስራ አለመጀመሩን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን #አስታውቋል።
የደረሰውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማጣራት የተቋቋምው ኮሚቴ ወደ ቦታው ለመደረስ አለመቻሉን የኮሚሽኑ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ሃላፊ ኮሚሽነር ዶክተር #አታክልቲ ገብረህይወት አስታውቀዋል።
ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ምርመራውን #እንደሚጀምርም ጨምረው ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27