YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#Ethiopia #Eritrea #የኢትዮ_ኤርትራን ግንኙነት ማጠናከርን ዓላማው ያደረገ ታላቅ ሩጫ በመቀሌ ከተማ ሊካሄድ ነው⬇️⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ የሁለቱን ሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር የታላቁ ሩጫ ውድድር በመቀሌ ከተማ ሊካሔድ ነው።

ሩጫውን የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ከኤርትራ አትሌቲክስ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት የሚያዘጋጁት መሆኑም ተመልክቷል።

የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኢዜአ እንዳስታወቀው ሩጫው የፊታችን ጥቅምት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ይካሄዳል።

ምንጭ፡ ኢዜአ
@YeneTube @Fikerassefa