YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሰበር ዜና

📌የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ አየር ኃይል ስኳድሮን በአሸባሪው አልሻባብ ሰራዊት ላይ ድልን ተቀዳጀ፡፡

📌ሰሞኑን አልሻባብ በአሚሶም ጥላ ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሰራዊት ለማጥቃት ሞክሮ እንደነበር የተነገረ ሲሆን ሰራዊቱ ለመቀያየር በጎዞ ላይ እንደነበር ተነግሮዋል፡፡

📌ይህንን ተከትሎ ታዲያ አየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃ በአልሻባብ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ገልጸዋል፡፡

📌እንዲሁም ከ70 በላይ የአልሻባብ አባላትና ከባድ መሳሪያ የጫኑ ሁለት ተሸከርካሪዎች አየር ኃይሉ ማውደሙም ተነግሮዋል፡፡

📌ብርጋዴር ጀነራሉ ከስምሪት በፊት ቡድኑን ለማጥቃት ከፍተኛ ጥናት መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

📌ጥናቱንም ተከትሎ በወሰደው እርምጃ መቶ በመቶ በሚባል ደረጃ ግቡን መምታቱንም አንስተዋል፡፡

📌ብርጋዴር ጄነራሉ የምድርና የአየር ኃይሉ ጥምረት አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቅሰው ይህ ጥምረትም ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡

📌በሌሎች አካባቢዎች ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት ያለብዙ ኪሳራና ወጪ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መመከት ይገባል ብለዋል፡፡
©fbc
@yenetube @mycase27
#ሰበር ዜና

9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ወደ #ነገ ተራዘመ

በዛሬው ዕለት ይጀምራል ተብሎ የነበረው 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባኤ ለነገ መራዘሙ ተገለፀ።
©fbc
@yenetube @mycase27