ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የኢትዮጵያ መንግስት በሶማሌ ክልል ለዓመታት ሲፈጸሙ በቆዩ የመብት ጥሰቶች እና ህገወጥነቶች ላይ ምርመራ ለማካሄድ ቁርጠኛ መሆን አለበት" ሲል አሳሰበ።
የምርመራ ሂደቱ የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት #አብዲ መሀመድ ዑመር እና አሁንም የክልሉ ልዩ ፖሊስ ኃላፊ የሆነውን #አብዱራህማን አብዱላሂ ቡረሌን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ሚና በጥልቀት የሚመረምር መሆን እንዳለበትም ጠቁሟል።
ተቋሙ በመግለጫው "የኢትዮጵያ መንግስት፣ በዓለምአቀፉ ህግ መሰረት የጦር ወንጀል የፈጸሙ የመከላከያ አባላትን እና ግለሰቦችን መርምሮ ለህግ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
የሰብአዊ ወንጀል እና ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ግለሰቦች በይቅርታ ሊታለፉ አይገባም" ብሏል።
ምንጭ ፦ ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27