Forwarded from YeneTube
ናቲ ስፒች ላንጉጅ ቴራፒ ኪሊኒክ
Nati Speech language therapy clinic
ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?
እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ
“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”
👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52
👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19
👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉 የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY
👂👂በነፃ
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ

❤15👀2
Forwarded from HuluGames Community
🥊 Man United Vs Arsenal 🥊
ማንችስተር ዩናይትድ ወይስ አርሰናል? 🏆
በትክክል ያገኙት ሁሉ ሽልማት ይኖራቸዋል! 🎁
📢 በነጻ ሁሉጌምስ ባትል ይቀላቀሉ!
⚽ ጨዋታውን ይገምቱ!
🏆 ያሸንፉ!
ሁሉጌምስ ባትል፣ በሁሉጌምስ ብቻ!! 🎮
🚀 ውድድሩን አሁኑኑ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ እና ግምትዎን ያስቀምጡ!
👇👇👇
Join Hulugames Battle
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍8❤5
ሽሬ ከተማ የቀጠናው የህገጥ ወርቅ ገበያ ማእከል መሆኗ ተገለፀ።
በከተማዋ ለሚገኝ የብሄራዊ ባንክ ቅርንጫፍ የሚቀርበው ወርቅ ከኮንጎ ጭምር የሚመጣ መሆኑ ነው የተገለፀው።ብሄራዊ ባንክ ለወርቅ አቅራቢዎች ከአለም ገበያ በላት እጅግ ሳቢ ክፍያ የሚፈፅም መሆኑ የቀጠናው ወርቅ ምርት ወደ ሽሬ እየገባ ለመንግስት እንዲሸጥ ማድረጉ ነው የተጠቀሰው።
በዚህም ከኤርትራ፣ ሱዳን እንዲሁም ኮንጎ ጭምር ወርቅ ወደ ትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ እየመጣ በአቅራቢዎች ለብሄራዊ ባንክ እንደሚሸጥ ተጠቅሷክ።ይሁንና ከነዚህ አገራት እና በኢትዮጵያ የሚገኙ ወርቅ አምራች ክልሎች ወደ ሽሬ የሚመጣው ጥራቱ የቀነሰ ወርቅ በትግራይ ከሚመረተው ጥራቱ ከፍ ያለ ወርቅ ጋር በመደባለቅ እንደሚሸጥ ነው የሚነገረው።ይህን ችግር ለመቅረፍ ማእከላዊ ባንኩ ጥረት መጀመሩ ነው በሪፖርተር ዘገባ የተገለፀው።
በተጠናቀቀው በጀት አመት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከ3.4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ከዚህም ውስጥ ምንጩ ከትግራይ የሆነው እጅግ ከፍተኛ ድርሻ የያዘ ነው።ነገር ግን የክልሉ ሀላፊዎች ከትግራይ ቀረበ በተባለው ወርቅ ላይ ሁሉም በክልሉ የተመረተ ነው ወይ የሚለው ላይ ጥያቄ አላቸው።
ሃለሰፊዎቹ ከትግራይ ቀረበ የተባለው ወርቅ ከተለያዩ ክልሎች እና ጎረቤት አገራት ጭምር ወደ ክልሉ መጥቶ የተሻለ ጥራት ካለው ምርት ጋር ተቀላቅሎ የቀረበ መሆኑን ይገምታሉ።ትግራይ ክልል አና የኤርትራ የጦር መሪዎች በዚህ ንግድ በጥምረት እንደሚሰሩ ነው ዘገባው ያከለው።
በ2017 ለብሄራዊ ባንክ የቀረበ ወርቅ
ትግራይ -39 ቶን
ጋምቤላ-5.4 ቶን
ኦሮሚያ-5.2 ቶን
ቤንሻንጉል ጉምዝ-4.7 ቶን
ሲዳማ-165 ኪግ
ምንጭ፡ ማእድን ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa

❤34😁10😭2👀1
አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈ!
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት በሙያው ሀገሩን አገልግሏል። ደበበ እሸቱ የመድረክ መሪ ፣ የሬዲዩ እና የቴሌቪዥን ድራማና ፊልሞች ተዋናይ እንዲሁም ጋዜጠኛም ነበር።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አንጋፋው የኪነ ጥበብ ሰው ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት በሙያው ሀገሩን አገልግሏል። ደበበ እሸቱ የመድረክ መሪ ፣ የሬዲዩ እና የቴሌቪዥን ድራማና ፊልሞች ተዋናይ እንዲሁም ጋዜጠኛም ነበር።
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
😭100❤23
በሕንፃዎችና በቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል መጠቀም አስገዳጅ ሊሆን ነው!
ኢትዮጵያ ያላትን የፀሐይ ኃይል ለመጠቀም በሁሉም ሕንፃዎችና ቤቶች ውስጥ የፀሐይ ኃይል መጠቀም በሒደት አስገዳጅ እንደሚሆን ተገለጸ፡፡ይህ የተገለጸው የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ (International Solar Alliance) ጋር የፀሐይ ኃይል በጋራ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ነሐሴ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ሲፈራረሙ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፀሐይ ኃይል አላት›› ያሉት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ደኤታ ሡልጣን ወሊ (ኢንጂነር)፣ ይህን አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል ከዚህ ቀደም አለመሠራቱን፣ ለዚህም ሲባል በሒደት በእያንዳንዱ ቤትና ሕንፃ ጣሪያ የፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂ እንደሚገጠም አስታውቀዋል፡፡
ተጨማሪ : https://ethiopianreporter.com/144548/

😁48❤29👎14😭5
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤2😁1
ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ!
ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡
በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።
ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።
ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።

👍39❤38😁10😭2
ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሺ በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ 541 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈጽሚያለሁ አለ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ አንድ ሺ 140 ለሚሆኑ ደንበኞቹ 541 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈጽሚያለሁ ሲል ገለጸ።
ከሐምሌ 22 እስከ ነሃሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት በአጠቃላይ ለባንኩ አንድ ሺ 140 ደንበኞች 541 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ፈቅጃለሁ ሲል በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾቹ ባጋራው መረጃ አስታውቋል።
በአንድ ቀን ብቻ ማለትም ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞች ማመልከቻዎችን ሁሉንም ማጽደቁን የጠቆመው ባንኩ በዚህም የ420 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች መፍቀዱን አመላክቷል።
ባንኩ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ ከአንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ መፈጸሙንም አስታውቋል።
ይህም የተሰጠው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ የተሰጠ መሆኑን ጠቁሟል።
Via AS

❤26😁13
ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ዮናስ አማረ ያሉበትን ሁኔታ መንግስት በግልፅ እንዲያሳውቅ ኢዜማ እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጠየቁ!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር፤ ጋዜጠኛ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ “ከሕግ አግባብ ውጪ መሰወራቸውን” በመግለጽ ያሉበትን ሁኔታ መንግስት በግልፅ እንዲያሳውቅ በተናጥል ባወጡት መግለጫ ጠየቁ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበርም በበኩሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ "ጋዜጠኞቹ በወንጀል ተጠርጥረው ቢሆን እንኳን በሕግ አግባብ ተይዘው በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ያሉበት አለመታወቁ በእጅገ ያሳስበናል" ብሏል።
ኢዜማ በበኩሉ፤ "በመንግሥት በኩልም በተደጋጋሚ ያለአግባብ ያሠርኩት ጋዜጠኛም ሆነ ዜጋ የለም የሚል ምላሽ ሲሰጥም ተመልክተናል" ሲል ጠቅሶ፣ “መንግሥት ድርጊቱን እየፈፀመ እየደበቀው ወይም ከመንግሥት እውቅና ውጪ በሌሎች የተደራጁ አካላት እየተፈፀመ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ብሏል።

❤29👀4👍3
በምዕራብ ትግራይ ወደ ቀያቸው በተመለሱ ተፈናቃዮች ላይ የመንግስት ወታደሮች ተሳታፊ የሆኑበት ግድያ እና አፈና እየተበራከተ ይገኛል ሰል ህወሓት አስታወቀ!
ወደ ቀያቸው በተመለሱ የምዕራብ ትግራይ ጸለምት ወረዳ ተፈናቃዮች ላይ “የኢትዮጵያ መንግስት ሰራዊት ተሳታፊ የሆነበት ግድያ እና እገታ እየተበራከተ ነው” ሲል ህወሓት ከሰሰ።
በምርጫ ቦርድ ምንም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ እግድ የተላለፈበት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ነሃሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫው፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ከለላ እሰጣችኋለሁ ብሎ እንዲመለሱ ባደረጋቸው የጸለምት ነዋሪዎችን ሊከላከልላቸው አልቻለም" ሲል ተችቷል፤ “ከሌሎች ታጣቂዎች ሊከላከልላቸው ይቅር እና እራሱ ተሳታፊ ሆኗል” ሲል ገልጿል።
“በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ባሳለፍነው ሳምንት በማይጸብሪ የተፈጸመው ግድያ የቅርብ ማሳያ ነው” ሲል በመግለጫው አመላክቷል።

❤20😭8👎5👀2😁1
Forwarded from Nati Getnet
ናቲ ስፒች ላንጉጅ ቴራፒ ኪሊኒክ
Nati Speech language therapy clinic
ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?
እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ
“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”
👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52
👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19
👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉 የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY
👂👂በነፃ
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ
Nati Speech language therapy clinic
ከእርስዎ ወይም ከቤተሰብዎ ከንግግር ጋር በተያያዘ ችግር ያለበት ሰው ያውቃሉ?
እንግዲያውስ ናቲ የንግግር የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ለእርስዎ የሚሆን መፍትሔ ይዞልዎት መጥቷል ከንግግር ከቋንቋ እንዲሁም ከተግባቦት ጋር በተያያዘ ህክምና ወይም ስልጠና ከፈለጉ ወደ ናቲ የንግግርና የቋንቋ ሕክምና እና ማማከር ክሊኒክ ይምጡ ወይንም ይደውሉ እፎይ የሚሉበትን ምላሽ ያገኛሉ
“አለመናገር ጨዋነት አይደለም እክል እንጂ”
👉አድራሻ፡ መገናኛ ሾላ አባይ ባንክ የካ ሚካኤል ቅርንጫፍ ያለበት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205
ከመምጣትዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
☎️ስልክ፡- 09- 08- 78- 26 -52
👉በተጨማሪም በነዚህ አማራጮች ያገኙናል
👉የቴሌግራም ገጽ ፡- https://tttttt.me/Nslt19
👉የቲክቶክ ገጽ፡-https://vm.tiktok.com/ZM69FtgrR/
👉 የፌስቡክ ገጽ፡-https://www.fb.com/l/6lp1kJRRR
👉በ YouTube ገፅ:-https://youtube.com/@natigetnet1989?si=_81wKG_5Ev45AZvY
👂👂በነፃ
የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በየትኛውም ክልል ለሚኖሩ በነፃ
❤6
በአዲስ አበባ ቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች እየታሸጉ መሆኑ ተነገረ
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የቢንጎ ማጫወቻ ቤቶች፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታሸጉ መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በወጣቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ እነዚህ ቤቶች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ፣ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ይህ መታሸግ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋለ ቢሆንም፣ በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የሚገኙ በርካታ የቢንጎ ቤቶች በዛሬው ዕለት መታሸጋቸው ካፒታል ተመልክቷል።
አንዳንድ የጨዋታ ቤቶቹ ባለቤቶች እንደተናገሩት፣ መታሸጉ የተፈጸመው “አዋኪ ድርጊት” ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ነው። በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እነዚህ አጫዋቾች፣ እርምጃው ቀጣይነት እንደሚኖረው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
ምንም እንኳ እነዚህ ቤቶች ዋነኛ ተግባራቸው የቢንጎ ጨዋታ ማቅረብ ቢሆንም፣ ከጨዋታው በተጨማሪ የጫት መጠቀሚያ እና ለህገወጥ ወንጀሎች መነሻ ቦታዎች እንደሆኑ እና ይህንንም መንግስት ለማስቆም በሚል እርምጃውን እየወሰደ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
በተለይ በአዲስ አበባ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በስፖርት ውድድር ላይ የሚደረጉ የውርርድ (ቤቲንግ) ጨዋታዎችን ከማሸግ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ እንዲገኝ የሚታወቅ ሲሆን አሁን የቢንጎ ቤቶች መታሸግ ከዚህ ጋር ግንኙነት ያለው ስለመሆኑ ግን እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር የለም።

❤37👍12👎2
ሀገራችን ኢትዮጵያ የራሷን ጦርነት ሳትቋጭ የፕሮክሲ ጦርነት ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።
የሱዳን እርስ በእርስ ጦርነት ስንት ሀገሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ ?
https://youtu.be/rs3JTbs89vg

YouTube
የሱዳን እርስ በእርስ ጦርንት ስንት ሀገሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ
#sudan #ethiopia #habesha #warzone #sudanwar
❤11😁11👍1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤1
YeneTube
Photo
ለዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች እየቀረበ ያለዉ ሀይል ተፅዕኖ እያሳደረበት እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት ገለፀ
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልገሎት ወደ ሶስት ያህል ለሆኑ የዳታ ሴንተሮች ሀይል እያቀረበ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ለእነዚህ የዳታ ሴንተሮች ከ 10 እስከ 20 ሜጋ ዋት ሀይል እየወሰዱ እንደሚገኝ ተቋሙ የተጠናቀቀው በጀት አመት የስራ አፈፃፀም እና የ2018 አመት እቅዶቹ ዙሪያ ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ስራ አስፈፃሚዉ ይህንን የገለፁት።
የዳታ ማይኒንግ ዘርፍ ላይ ለሚገኙ ድርጅቶች ከፍተኛዉን ሀይል እያቀረበ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል መሆኑን የገለፁት ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ለድርጅቶቹ የሚቀርበዉ ሀይል ከፍተኛ መሆን በአገልግሎቱ ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪፖርት እንደተገለፀዉ ከሆነ በተጠናቀቀው በጀት አመት አገልግሎቱ 16 ሺህ 2 መቶ 43 ጌጋ ዋት ሀይል ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በጅምላ መግዛቱን ያሳያል።
ይህ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የሀይል ፍላጎቱ 18.2 በመቶ ከፍ ማለቱን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ መንግስት በዳታ ማይኒግ ዘርፍ ለሚሰማሩ ድርጅቶች በቀጣይ የሚሰጠዉ ፍቃድ አለመኖሩን አስታዉሰዉ።
ሆኖም በአገልግሎቱ ላይ ለድርጅቶቹ እየቀረበ የሚገኘዉ ሀይል ተፅዕኖ መኖር በግልፅ የሚታይ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በበኩሉ በበጀት አመቱ ከዚህ ዘርፍ የመጣው ገንዘብ በተቋሙ አጠቃላይ ገቢ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘ መሆኑን ይገልፃል።
ለመደበኛ ተጠቃሚዎች የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ ከተገኘው ገቢም የሚበልጥ መሆኑን ገልፆል።
ነገር ግን ከአሁን በኋላ ለአዲስ የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች ፈቃድ እንደማይሰጥ እና ያሉትም በሂደት እንዲወጡ የመግፋት ፍላጎት እንዳለው ይፋ አድርጓል።
@Yenetube @FikerAssefa

❤10👍7😁6
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል - የገንዘብ ሚኒስቴር
የገንዘብ ሚኒስቴር በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል አለ፡፡
ነባሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ከምጣኔ ውጭ ሌሎች ማሻሻያዎችን በማካተት ከ3 አስርት ዓመታት በኋላ ተሻሽሎ በ2017 በጀት አመት ስራ ላይ መዋሉን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
የታክስ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከነበረው ከ12 በመቶ በላይ ድርሻ በየዓመቱ በተከታታይ እየቀነሰ ከ7 በመቶ በታች መድረሱን ጠቅሶ፥ ከዚህ ጠቅላላ ቅናሽ 44 በመቶው የተጨማሪ እሴት ታክስ ድርሻ እንደሆነ አመልክቷል፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ህጉን አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ የቀጣይ ዓመታት ለውጦች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ በመካከለኛ ዘመን የገቢ ስትራቴጂው መሰረት ተሻሽሎ በ2017 በጀት ዓመት ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብሏል፡፡
በማሻሻያው መሰረት በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ማሻሻያ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን ነው የገንዘብ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

❤14👍8😁1