YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
4 ቢሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን አስታወቀ!

ኮሚሽኑ በተቋሙ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ያለው የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል፡፡ኮሚሸኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በ2017 በጀት አመት 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል ይህም ካለፈው አመት ጋርሲነጻጸር የ2.2 በመቶ እድገት አሳይቷል።

በበጀት አመቱ ለ 525 አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች ፈቃዶች እና 19 የማስፋፊያ ፈቃዶች መሰጠቱን ጠቁሞ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከወሰዱት ውስጥ የውጭ ባለሃብቶች 308፣ 109 ለጣምራ ኢንቨስትመንት እና ከ98 በላይ ደግሞ ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሊሰጥ ችሏል። ይህም በተቋሙ ታሪክ ትልቁ ቁጥር ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል።

በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ባሉ ኢንቨስትመንቶች 123 ሚሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ገቢ ያስገኙ ሲሆን ከዞኖቹ ውጪ ባሉ ኢንቨስትመንቶች 543.11 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል።ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው በ2017 በጀት አመት ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች በመተካት ስኬት እንዳስመዘገበ ገልጿል።

@YeneTube @FikerAssefa
16😁11🔥2👎1
YeneTube
Photo
ወደ ሶማሊያ ሲጓዝ በፑንትላንድ ሀይሎች ተይዞ የነበረውና የተለቀቀው የጦር መሳሪያ የጫነ መርከብ አቅጣጫውን ወደ ጅቡቲ ቀይሮ መጓዙ ተነገረ!

“ሲ ወርልድ” የተሰኘው መርከብ በቅርቡ የጦር መሳሪያ ጭኖ ከቱርክ፥ ኢዝሚር ግዛት ወደ ሶማሊያ ሲጓዝ፥ በሶማሊያ ሰሜናዊ ግዛት በፑንትላንድ ሀይሎች ተይዞ ከተለቀቀ በኋላ፥ አቅጣጫውን በመቀየር ወደ ጅቡቲ መጓዙን ከስፍራው የወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። የመጀመሪያ መድረሻው ሞቃዲሾ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በአቅራቢያው ወደምትገኘው ጅቡቲ አቅጣጫውን ቀይሯል።

የጭነት መርከቡ በፑንትላንድ የባህር ኃይል ፖሊስ (PMPF) ተይዞ መክረሙ ከሰሞኑ ሲዘገብ ቆይቷል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ መርከቡ የጦር መሳሪያ እገዳ ከጥቂት አመታት በፊት የተነሳላት የሶማሊያን ዋና ከተማ ሞቃዲሾ አቅጣጫ አድርጎ እየተጓዘ ነበር።

በወቅቱ የወጡ ተጨማሪ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የጦር መሳሪያው በሶማሊያ “TURKSOM” በመባል በሚታወቀው ወታደራዊ ካምፕ የሚውል ነው። “TURKSOM” የሶማሊያና ቱርክ ጥምር ወታደራዊ ማሰልጠኛ በአል-ሻባብ ላይ በሚደረገው ውጊያ ለሚሰለጠኑት የ “ጎርጎር” ወታደሮች ማሰልጠኛ ስፍራ እንደሆነ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ፣ በርካታ በሱማሊያ የሚሰራጬ ዘገባዎች፣ መርከቡ በወቅቱ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ሞቃዲሾን ትቶ አቅጣጫውን ወደ ጅቡቲ መቀየሩን ጠቁመዋል።
ሞቃዲሾም ሆነ አንካራ እስካሁን ባለው ሁኔታ ላይ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጡም።

ከሶስት ሳምንታት በፊት የፑንትላንድ የባህር ኃይል ፖሊስ በኮሞሮስ ባንዲራ ስር ይጓዝ የነበረውን ይህን  “ሲ ወርልድ” የተባለ የጭነት መርከብ ከቱርክ የተላከ ወታደራዊ መሳሪያ ጭኖ ለሶማሊያ ጦር (SNA) ለማድረስ በሚል ሲጓዝ በቦሳሶ ወደብ ነበር የተያዘው ።

በፑንትላንድ ባለስልጣናት መግለጫ መሰረት፣ የቱርክ አምባሳደር ወደ ሶማሊያ ባደረጉት ጉብኝት፣ በመርከቡ ላይ ያለው የጦር መሳሪያ፣ የቱርክ መንግስት ንብረት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካቀረቡ በኋላ የፑንትላንድ ባለስልጣናት መርከቡን ለመልቀቅ ወስነዋል።ነገር ግን፥ ትላንት የወጣው የጋሮዌ ዘገባ መርከቡ ለምን ወደ ጅቡቲ እንዳቀና አልገለጸም።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
24👍1
ሂልተንን ጨምሮ አራት ሆቴሎች 564 ሚሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገቡ!

ሂልተን ሆቴልን ጨምሮ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚተዳደሩ አራት የቱሪዝም ዘርፍ ድርጅቶች፣ በ2017 የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 564.2 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተገለጸ። ይህ ውጤት ከታቀደው የትርፍ ግብ በ37 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባደረገዉ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ፣ የስፓ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ (ፍል ዉሃ)፣ የጊዮን ሆቴሎች ኢንተርፕራይዝ፣ ሂልተን ሆቴል እና የገነት ሆቴልን ያካተተውን የሆቴል ዘርፍ አፈጻጸም ላይ ትኩረት አድርጓል።

ድርጅቶቹ በድምሩ 2.1 ቢሊዮን ብር ገቢ በማሰባሰብ ከታለመው 114 በመቶ ማሳካት ችለዋል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ እያደገ የመጣውን የገበያ ፍላጎት እና የቱሪስቶች ፍሰት በመጠቀም ንግዳቸውን እንዲያሰፉ አሳስቧል።

ለዘላቂ እድገት ሲባልም የደንበኞችን እርካታ ማሻሻል፣ ዘመናዊ የግብይት ስልቶችን መጠቀም፣ እንዲሁም ዲጂታል አገልግሎትና የቦታ ማስያዣ ስርዓቶችን ማዘመን እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ተሰጥቷል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
11😁5👍3👎3🔥1
ብሔራዊ ቲያትር የቲኬት ዋጋን ወደ 200 ብር አሳደገ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር የመግቢያ ትኬት ዋጋን ከ ስምንት ዓመት በፊት ከነበረበት 80 ብር ወደ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል። ቲያትሩ ከ1948 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ኪነጥበብ ከፍ ማለት እና መከበር አለበት በሚል ዋጋዉን ለማሻሻል ጥናት ሲደረግ መቆየቱ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ የኪነጥበብን ደረጃ ከፍ ለማድረግ እና የቲያትር ቤቱን አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች፣ የቲኬት ዋጋው ከዚህ ቀደም በጣም ዝቅተኛ ስለነበር፣ አሁን የተደረገው ጭማሪ ሳይሆን 'ማሻሻያ' ነው ሲሉ አብራርተዋል። የዋጋ ማሻሻያው "ማንንም የማይጎዳ መልኩ" መሆኑን በማስረገጥ፣ የቲኬት ዋጋው ለሁሉም ትያትሮች በ200 ብር መወሰኑን ገልጸዋል።

ኦንላይን ትኬት ሽያጭ እና ሌሎች ለውጦች
ከተመሠረተ 70 ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ ቲያትር፣ አዳዲስ ለውጦችን በማምጣት ተመልካቹን ለማርካት መዘጋጀቱን አስታውቋል።ከለውጦቹ መካከል ተመልካቾች ከየቤታቸው ሆነው ትኬት መግዛት የሚያስችላቸውን 'ኦንላይን' የቲኬት ሽያጭ ሥርዓት ማመቻቸቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም፣ የቲያትር ቤቱ ኃላፊዎች በቀጣይ ሁሉም ክልሎች የሚሳተፉበት ሥልጠና በብሔራዊ ቲያትር እንደሚሰጥ አስታውቀዋል። ይህ የዋጋ ማሻሻያ እና ሌሎች ተያያዥ ለውጦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማምጣት እና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

@YeneTube @FikerAssefa
37👎5😁3