ልዩ መረጃ
የሱዳን ጦር በሱዳን ዳርፉር በኒያላ አየር ማረፊያ ሲያርፍ የነበረ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አይሮፕላን ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተሰማ።
የሱዳን ጦር የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አውሮፕላን በዳርፉር ግዛት ስትራቴጅካዊቷ ኒያላ ከተማ ሲያርፍ ኢላማ አድርጓል ሲል የሱዳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አውሮፕላኑ የኮሎምቢያ ቅጠረኛ ተዋጊዎችን ይዞ እንደነበር እና ሲያርፍ በትናንትናው ዕለት August 6/2025 በሱዳን ጦር ጥቃት እንደደረሰበት ዘገባው ጠቅሷል። በጥቃቱ ከ40 በላይ የኮሎምቢያ ቅጥረኛ ወታደሮች/Colombian mercenaries/ መሞታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ኒያላ አየር ማረፊያ በጄኔራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ቁጥጥር ስር ይገኛል።
የሱዳን ጦር አረብ ኢምሬትስ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ድጋፍ ታደርጋለች ብሎ ያምናል።
አዩ ዘሀበሻ
@Yenetube @Fikerassefa

❤23👍6🔥1
የኢትዮጵያ ጦር ለሶማሊያ ወታደሮች ሰጠ የተባለው ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?
በሶማሊያ ጌዶ ክልል የሚገኘው የኢትዮጵያ ሠራዊት የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ወታደሮች በቅርቡ ከያዙት የድንበር ከተማ፣ በለድ ሀዋ በሦስት ቀን ውስጥ ለቅቀው እንዲወጡ ለአገር ሽማግሌዎች መናገራቸው ተገለፀ።
ከተማዋ በለድ ሀዋ ቁልፍ የሶማሊያ የድንበር ከተማ ስትሆን ኢትዮጵያን እና ኬንያን የምታዋስን እና የኢትዮጵያ ሠራዊት የሚገኝባት ነች።
ባለፉት ሳምንታት የሶማሊያ የከፊል ራስ ገዝ ክልል ጁባላንድ ታጣቂዎች እና የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ወታደሮች በአካባቢው ውጊያ አካሂደው፣ የሶማሊያ መንግሥት ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም. ከተማዋን በቁጥጥሩ ስር አውሏል።
ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮንኖች ከሶማሊያ የጎሳ መሪዎች ጋር በዶሎ ከተማ መነጋገራቸውን እና የሶማሊያ ፌደራል መንግሥቱ ወታደሮች ከበለድ ሀዋ በሦስት ቀን ውስጥ ለቅቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የአገር ሽማግሌዎች ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።
በሶማሊያ የፌደራል መንግሥት የጌዶ አስተዳዳሪ የሆኑት አብዱላሂ አብዲ ጃማ (ሺምቢር) በዶሎ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሠራዊት በበለድ ሀዋ የሚገኘውን የሶማሊያ መንግሥት ኃይል በሦስት ቀናት ውስጥ ለቅቆ እንዲወጣ በአገር ሽማግሌዎች እንደተነገራቸው ገልፀዋል።
የጌዶ አስተዳዳሪ አብዱላሂ አብዲ ጃማ (ሺምቢር) ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በጥምረት የሚሠራ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ሠራዊት በኩል ተላለፈ በተባለው ትዕዛዝ ምክንያት ከበለድ ሀዋ የሚወጣ የፌደራል ጦር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
👇👇
https://www.bbc.com/amharic/articles/c5y3edzy2zyo
@YeneTube @FikerAssefa

1❤21😁4👍1
YeneTube
Photo
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ካመነጨሁት ሀይል 33.2 በመቶው የተገኘው ከህዳሴ ግድቡ ነው አለ።
በበጀት ዓመቱ ከተገኘው ሀይል 93 በመቶው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የተቀረው 7 በመቶ ደግሞ ለውጪ ሀገራት የተሸጠ መሆኑ ተነግሯል።
ተቋሙ ይህንን ያለው የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን እና የ2018 በጀት ዓመት እቅዱን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው።በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 29,480 ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨቱን ተናግሯል።
ይህም ካቀድኩት በላይ ነው ያለው ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 25,423 ጊጋ ዋት ሰዓት የማምረት እቅድ ነው የነበረኝ ብሏል።ከሀይል ሽያጩ 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ ተናግረዋል።
ከመነጨው ሀይልም 33.2 በመቶው የተገኘው ከህዳሴ ግድቡ መሆኑን ያብራሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንጅነር አሸብር ባልቻ 93 በመቶው የመነጨው ሀይል ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የተቀረው 7 በመቶ ደግሞ ለውጭ ሀገራት የተሸጠ ነው ብለዋል።ለሀገር ውስጥ ከቀረበው 93 በመቶ ሀይል 60 በመቶው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተሸጠ፣ 27 በመቶው ለዳታ ማይኒንግ እና 6 በመቶው ደግሞ ለኢንዱስትሪዎች የተሸጠ መሆኑን ከተቋሙ ሰምተናል።
ከአጠቃላይ የመነጨ ሀይል 7 በመቶው ለውጭ ሽያጭ መቅረቡን ያስረዱት ሀላፊው ለውጭ ሀገራት በሽያጭ ከቀረበው 5 በመቶው ለኬኒያ እና 2 በመቶው ለጅቡቲ እንደተሸጠ ተናግረዋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በተጠናቀቀው በጀት አመት ችግር ሆነውብኛል ስላላቸው ጉዳዮችም አንስቷል።
የመሰረተ ልማት ስርቆት ሲፈትነኝ ቆይቷል ያለው ተቋሙ፤በ43 የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶብኛል ብሏል።በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦት እንደልብ ስራዎችን ተዘዋውሬ መስራት እንዳልችል ያደረገኝ ሌላኛው ችግር ነው ሲል ተናግሯል።
Via Sheger

😁24❤20👍2
በሲዳማና ኦሮሚያ ድንበር አከባቢ የተከሰተው አለመግባባት የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ
ነሀሴ 1/2017 የሲዳማ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
በሲዳማና ኦሮሚያ ድንበር አከባቢ የተከሰተው አለመግባባት የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ። የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ዳንጊሶ እንደገለጹት በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በበንሳና በቡራ ወረዳዎች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በኮኮሳና ላንሳቦ ወረዳዎች አካባቢ በጥቂት ግለሰቦች መካከል አለመግባባት መፈጠሩንና የከፋ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን ገልፀዋል ። አለመግባባቱ በጥቂት ግለሰቦች መካከል የተፈጠረ ክስተት መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል።
አለመግባባት ሊከሰት የሚችል ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የቢሮ ኃላፊው የተፈጠረውን ክስተት የሲዳማና የኦሮሚያ ክልል የዞንና የወረዳ አመራሮች ሁለቱን ወገኖች በማነጋገር በእርቅ ለመፍታት በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል ።
በተያያዘም DW Amharic ከጉዳዩ ጋር አያይዞ ያሰራጨው ዘገባ ተዓማኒነት የጎደለውና የሚዲያ ሥነ_ምግባርን የጣሰ መሆኑን እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ ጋር የሚያጋጭ ስለሆነ ከድርጊቱ ሊቆጠብ ይገባል ብለዋል።

❤34👍12😁4🔥1
በአመቱ ከዴታ ማይኒንግ የተገኘው ገቢ ግንባር ቀደም ነው!
የዴታ ማይኒንግ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ እየገቡ መስራታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ገቢ እያገኘ መሆኑ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡በተለይ በማይኒንግ ስራ የተሰማሩት ኩባንያዎች የሚከፍሉት በውጭ ምንዛሬ መሆኑ ለሃይል አቅራቢው ትልቅ እድል የፈጠረ ነው፡፡
በ2017 መጀት አመት ከአገር ውስጥ የሃይል ሽያጭ ከተገኘው 75.4 ቢሊየን ብር ገቢ የ39 በመቶ ድርሻ የነበረው የዴታ ማይኒንግ ኩባንያዎች ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ሃይል ለሚያቀርበው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተሸጠው የተገኘው የ35 በመቶ እንዲሁም የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች የ4 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡
ሆኖም ለሽያጭ ከቀረበው ኃይል ውስጥ በመጠን ከፍተኛውን የወሰደው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሲሆን 60 በመቶ ነው፡፡የዳታ ማይኒንግ 27 በመቶ፣ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች 6 በመቶ ፣ ኬኒያ የ5 በመቶ እንዲሁም ለጅቡቲ 2 በመቶ እንደቀረበ ነው የሃይል አምራች ሻጩ የገለፀው።
[KGEthiopia]

❤15😁9⚡1🔥1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤2
Forwarded from YeneTube
በ 25% ዲስካውንት ለገበያ አቅርበናል!
📌 ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
✅ መገልገያዎች
👉 ሦስት ሊፍት
👉 ባለ 3 ፎቅ የመኪና ማቆሚያ ቦታ
👉 ቴራስ
👉 ያልተገደበ የውሃ አቅርቦት
👉 የመጠባበቂያ ጀነሬተር
📌 የካሬ አማራጮች
👉ባለ 1መኝታ - 63 ካሬ
👉ባለ 2 መኝታ - 86 እስከ 103 ካሬ
👉ባለ 3 መኝታ - 132 እስከ 146 ካሬ
👉1 መኝታ 63ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 86 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር
👉3መኝታ 114 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር
ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር
ለበለጠ መረጃ
☎️ +251976195835
Telegram username
@Ruthtemersales
What's app
https://wa.me/251976195835
TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate

❤1
Forwarded from ALX Ethiopia
🚀 Want to become a Virtual Assistant? Join our live Telegram session to learn about the programme, how to apply, and get your questions answered!
Don’t miss it - happening this Saturday, 3 ነሐሴ 2017 (August 9, 2025) starting at 11፡00 (5:00 PM) in our Telegram group
👉🏾 t.me/virtualassistantapplicationguide
#ALXEthiopia #ALXAfrica #ALXTribe #AIwithALX #VirtualAssistant

❤4
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል በነበረው ውይይት ላይ ከሁለት ፖርቲዎች ውጪ ሁሉም ፖርቲዎች መሳተፋቸውን ገለጸ!
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ባካሄደው ውይይት ላይ ከሁለት ፖርቲዎች በስተቀር ሁሉም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች መሳተፋቸውን አስታውቋል።ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ምክክር ለመጀመር የሚያስችል ውጤታማ ውይይት መደረጉን በዛሬዉ ዕለት በሰጠው መግለጫ ላይ የገለጸ ሲሆን፤ "የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 'የሀገራዊ ምክክር ሥራውን በበጎ እንደሚመለከተው' አስታውቋል"ም ብሏል።
በመግለጫውም በትግራይ አጀንዳ ማሰባሰብ የሚያስችል ሥራ ለመስራት የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ ቆይቶ፤ ሐምሌ 22 ለመጀመሪያ ጊዜ በትግራይ በመገኘት ውይይት ማካሄዱን የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ጥበብ ታደሰ ተናግረዋል።ኮሚሽኑ በትግራይ ከጊዚያዊ አስተዳደር፣ ከፖርቲዎች፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ጋር ውይይት ማካሄዱንም ገልጸዋል።
በውይይት ወቅት በርካታ ጉዳዮች ከተሳታፊዎች መነሳታቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፈጸም፣ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲመለስ እንዲሁም፤ በትግራይ ከጦርነቱ በፊት ወደነበረችበት ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት እንድትመለስ የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በአሁን እያንዣበበ ያለው የጦርነት ሁኔታ መፍትሄ እንዲበጅለትም ከተጠየቁ ጉዳዮች መካከል እንደሚገኙበት አንስተዋል።"ይሁን እንጂ በትግራይ በኩል የቀረቡት እነዚህ ሁኔታዎች ምክክር ለማካሄድ ቅድመ ሁኔታዎች አይደሉም" ያሉት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ፤ "ለምክክር ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ አያስፈልገውም" ብለዋል።
"ኮሚሽኑም የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የሀገራዊ ምክክር ሥራውን በበጎ ይመለከተዋል" ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
አሐዱም "በትግራይ በነበረው ውይይት ምን ያህል የፖለቲካ ፖርቲዎች ተሳትፈዋል?" ሲል የኮሚሽኑን ቃል አቀባይ ጠይቋል።
ቃል አቀባዩ አቶ ጥበቡ ታደሠ በሰጡት ምላሽ፤ በትግራይ ክልል በነበረው ውይይት ከሁለት የፖለቲካ ፖርቲዎች ማለትም ከ'አረና ልዓላዊ ፖርቲ' እና 'ውድብ ናፅነት ትግራይ' ውጪ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፖርቲዎች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።
ቃለ አቀባዩ ይህንን ይበሉ እንጂ ባይቶና አባይ ፖርቲ እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይን የመሱሉ ፖርቲዎችም፤ በመቀሌ በነበረው ውይይት ላይ አለመሳተፋቸውን አሐዱ ከዚህ ቀደም መዘገቡ ይታወሳል።
የሀገራዊ ምክክር ክሚሽን የተለያዩ ግብዓቶቸን በመውሰድ ተከታታይነት ያለው ውይይት በማድረግ በትግራይ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱን ለማከናወን አጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።
ኮሚሽኑ በዛሬው መግለጫው "በትግራይ ክልል ወደ ሃይል አማራጭ የሚሄዱ አካላቶች ከድርጊታቸወሰ እንዲቆጠቡ" ሲል ጥሪ አቅርቧል።በመግለጫው የዲያስፖራ አጀንዳ ማሰባሰብ ሥራው መቀጠሉ የተነገረ ሲሆን፤ በነገው ዕለት በደቡብ አፍሪካ የአጀንዳ ማሳሰብ ሥራ እንደሚካሄድም ተገልጿል።
Via Ahadu

❤19😁6
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለአፍሪካ ትልቁ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የገንዘብ አስተባባሪነትን በይፋ ተረከበ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና፣ የ7.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበትን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ በዋናነት እንዲያስተባብር የሚያስችለውን ስምምነት ሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአቡሴራ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ በየዓመቱ 60 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።ይህ አቅም ሙሉ በሙሉ ሲጠቀም እስከ 110 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን ማስተናገድ ይችላል። የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ የግንባታ ምዕራፍ እ.ኤ.አ. በ2025 መጨረሻ ላይ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
Via Capital

❤19👎13😭2🔥1
የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞቹ 914 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መስጠቱን ዳሸን ባንክ አስታወቀ!
ዳሸን ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ ደንበኞቹ 914 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 257 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ለነዳጅ ግዥ የቀረበ መሆኑን ገልጿል፡፡
ባንኩ እ.ኤ.አ በሃምሌ ወር 2025 ብቻ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞች 112 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማቅረቡን ጠቁሞ ከዚህም ውስጥ 33 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ለነዳጅ ግዥ ማቅረቡን አስታውቋል፡፡
ዳሸን ባንክ በዚሁ ወር 73 ነጥብ1 ሚሊየን ዶላር የተለያዩ ምርቶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እንዲውል ማቅረቡን ገልጾ ከዚህም በተጨማሪ ወደተለያዩ የውጭ አገራት ለሚጓዙ ደንበኞቹ 5 ነጥን 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መስጠት ችሏል፡፡
ባንኩ በያዝነው ወር የመጀመሪያ ስድስት ቀናት እንዲሁ የውጭ ምንዛሬ ጥያቄ ላቀረቡ ደንበኞች 11 ሚሊየን ዶላር ሰጥቻለሁ ብሏል፡፡ባንኩ ደንበኞቹ የሚያቀርቧቸውን የውጭ ምንዛሬ ጥያቄዎች ለማሟላት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

❤30👍1
የኢትዮጵያ የኢነተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር 55 ሚሊየን ደርሷል ተባለ!
ቁጥሩ የኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ ከመጀመሩ በፊት 17 ሚሊየን እንደነበር የኢኖቬሽና እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አማካሪ አቢዮት ባዩ ገልፀዋል፡፡
25 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ለፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ እንደተመዘገቡም አክለዋል፡፡ በ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ 1.8 ሚሊየን ዜጎች እየተሳተፉ እንደሆነ እና 1 ሚሊየን የሚሆኑት የእውቅና ሠርትፍኬት እንደተሠጣቸውም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በ2018 ዓ.ም ህዳር ወር ፊውቸር ቴክ ኤክስፖ 2025ን ታስተናግዳለች፡፡ ዝግጅቱ ስታርታፕችን ከኢንቨስተሮች ለማገናኘት እና የንግድ አጋርነቶችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡
Via Ethio FM

❤11😁3🔥1
በትግራይ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ 22 ሰዎች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ!
በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ያቄር ቀበሌ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ ከግንቦት ወር በኋላ 22 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በቀጣይ ሳምንታት እርዳታ የማይደርስ ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊያልቁ እንደሚችሉ የቆላ ተምቤን ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎይቶም ገብረ ሐዋርያ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከሰዎች በተጨማሪ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት መሞታቸውን ላላፊው ጨምረው አስታውቀዋል።
108 ሺህ አካባቢ ነዋሪዎች ካሏት የቆላ ተምቤን ወረዳ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ በከፋ ሁኔታ የተጠቃችው 4112 ነዋሪዎች ያሏት ያቄር የተሰኘችው ቀበሌ ናት።
ወረዳው በፊትም ቢሆን ድርቅ የሚያጠቃው አካባቢ ቢሆን በዘንድሮው ክረምት በተለየ መልኩ ዝናብ ባለመዝነቡ የተዘሩ ሰብሎች ለመብቀል ባለመቻላቸው የድርቁ መንስዔ እንደሆነ አቶ ጎይቶም ያስረዳሉ።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c62w8y75v67o

😭38❤19
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትግራይ ክልል 60 ሺህ ወጣቶች መሰደዳቸው ተሰማ!
የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ በተፈጠረው የከፋ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ በርካታ የትግራይ ወጣቶች ወደ ስደት እያመሩ መሆኑ ይገለፃል።ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከትግራይ የተለያዩ አካባቢ ወደ አረብ ሃገራት እንዲሁም በሊብያ በኩል ወደሚደረግ ስደት የሚያመሩ ወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የሚገልፀው የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በዚሁ ሂደት በሚፈጠሩ አደጋዎችም በሺህዎች የሚቆጠሩ መነሻቸውን ትግራይ ያደረጉ ወጣቶች ለሞት እየተጋለጡ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን አስታውቋል።
ከቢሮው የተገኘ መረጃ ባለፈው ዓመት እና በያዝነው 2017 ዓ.ም. ቢያንስ 60 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ከክልሉ ተነስተው ወደ ዓረብ ሃገራት እንዲሁም ወደ ሊብያ ማምራታቸው ያመለክታል። ከእነዚህ መካከል ሁለት ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች በስደት በሚያጋጥሙ መጥፎ ሁኔታዎች መሞታቸው መረጋገጡን የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ለዶቼቬለ እንዳሉት፥ በተደረገው ጥናት መሠረት 32 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ባለፈው ዓመት፣ በያዝነው ዓመት ደግሞ 28 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች መደበኛ እና ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ከትግራይ በመነሳት ተሰደዋል።
ሓላፊው «ይህ ቁጥር በጥናት የተረጋገጠ እንጂ፥ መረጃቸው ያልተገኘ በርካታ ወጣቶች መሰደዳቸውን መገንዘብ ይቻላል» ብለዋል።አቶ ሓይሽ ስባጋድስ «በስደት በተደጋጋሚ በሚከሰቱ አደጋዎች ምክንያት ሁለት ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን አረጋግጠናል» ሲሉ አክለው ገልፀዋል።ቢሮው ያደረገው ጥናት ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎች ያላካተተ እንዲሁም የመረጃዎች እጥረት ያሉበት በመሆኑ የሕገወጥ ስደቱ እና ሞት መጠኑ ከተጠቀሰው ሊበልጥ ይችላል ተብሏል።
የትግራይ ወጣቶች ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ለወጣቶች ስደት ሥራ አጥነት የመጀመርያው ምክንያት ነው፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ደግሞ በሁለተኛነት እንደሚጠቀስ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የደላሎች ማታለያዎች እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶችም ወጣቶችን ለስደት እየገፉ እንዳሉ ተመልክቷል።ከጦርነቱ በኋላ የተለየ ትኩረት በመስጠት በወጣቶች ሥራ ፈጠራ እንዲሁም ሌሎች ተስፋ በሚሰጡ ሁኔታዎች ላይ መሥራት አለመቻሉ ፍልሰቱ እንዲባባስ እንዳደረገውም ተገልጿል። የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሐላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ ችግሩን ለመፍታት ከፌደራል መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ እንደሚጠበቅ ያነሳሉ።
Via DW

❤24😭9👍3