'የነጻ መሬት ታጣቂዎች በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት ሰነዘሩ' - የትግራይ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ
የትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ታጣቂዎች ምላዛት በተባለው አካባቢ በሰፈረው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይል ላይ ጥቃት አድርሰዋል ሲል ከሰሰ።ቢሮው ሐሙስ ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ በአካባቢው በሚገኘው የትግራይ ታጣቂዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት አንድ አባል መሞቱን አስታውቋል።
ረቡዕ ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም. በተፈጠረው ግጭት የተገደለው የትግራይ ኃይሎች አባል አንዳይ ክንደያ የተባለ መሆኑንም ገልጿል።ትግራይ ክልል ከአፋር ጋር በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች እንደሚንቀሳቀሱ የሚነገርላቸው እና በተለምዶ "ሓራ መሬት" (ነጻ መሬት) ተብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች፣ ከትግራይ ኃይሎች ተነጥለው የወጡ ናቸው።
እነዚህ ታጣቂዎች በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ክንፍ እና ድርጅቱን የሚደግፉ የትግራይ ኃይሎች አዛዦች ከሥልጣን ለማስወገድ ወደ አፋር ክልል ሄደው መደራጀታቸውን ይናገራሉ።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa

❤27😁4😭3👎2👍1
ግብፅ እና አሜሪካ በውሃ ደህንነት እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙርያ መከሩ!
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ከግብጹ አቻቸው ባድር አብደላቲ ጋር በግብጽ የውሃ ደህንነት ዙርያ እንዲሁም በመካከላኛው ምስራቅ ሰላማን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታወቀ።
ሚኒስትሮቹ ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሩቢዮ፤ “ግብፅ በሐማስ ተይዘው የነበሩ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ላሳየችው ጽኑ ድጋፍ” ለአብደላቲ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስነብቧል።
በተጨማሪም በሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ስለሚደረገው ሽግግር አስፈላጊነትም ተወያይተዋል ሲል መስሪያ ቤቱ አክሎ ገልጿል።የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባድር አብደላቲ ስብሰባውን አስመልክቶ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በማጠናከር፣ ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች እና በግብፅ የውሃ ደህንነት ዙርያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይቱን ያካሄዱት በጋዛ ስላለው ረሃብ አስመልክቶ ከሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በኩል የሚደረጉ ጥሪዎች እየተበራከቱ በመጡበት በአሁኑ ወቅት ነው።
Via AS

👎22❤15👍1
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ከጠቅላላው የወጪ ንግዷ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ!
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ከጠቅላላው የወጪ ንግዷ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡በበጀት ዓመቱ ከጠቅላላው የወጪ ንግድ ገቢ 5.145 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘት መቻሉን ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቀዋል፡፡
ይህም በ2016 በጀት ዓመት ከተገኘው 3.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶለር ጋር ሲነፃፀር የ4.59 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 123.78 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ግብይት ማዕከላትን በ2016 ዓ.ም. ከነበረበት 1066 ወደ 1,300 ለማሳደግ ታቅዶ 501 አዳዲስ ገበያዎች በመክፈት 1,567 ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መንደር ተገንብቶ 5 ጥራት አስጠባቂ ተቋማትን በአንድ ቦታ በመያዝና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ቀጠናዊ ውህደት እና ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነትን ከማጎለበት አንጻር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ተግባራዊነት ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ አያይዘውም በ2018 በጀት ዓመት ስኬቶችን ለማስቀጠል እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡

❤10👎5👀5😁4🔥1
ተቃውሞ የቀረበበት ድንጋጌ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ እንዲወጣ ተደረገ!
አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ'ፖለቲካል አድቮከሲ' እና ከምርጫ ጋር የተያያዙ ስራዎችን ለመስራት ከውጭ የፋይናንስ ምንጭ ገንዘብ እንዳይቀበሉ የሚከለክለው ድንጋጌ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ማሻሻያ እንዲወጣ ተደረገ።
ቢቢሲ የተመለከተው የማሻሻያው 'የመጨረሻ ረቂቅ' አገር በቀል ድርጅቶች ማንኛውም ከምርጫ ጋር የተያያዘ ስራ ላይ ለመሰማራት "ቅድሚያ [ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች] ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ ማግኘት" እንዳለባቸው ያትታል።
ማሻሻያ እየተደረገበት የሚገኘው በስራ ላይ ያለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ የጸደቀው ከስድስት ዓመት በፊት ነበር።
አዋጁ ከ16 ዓመት በፊት ወጥቶ የነበረውን እና 'አፋኝ ነው' በሚል የሚተቸውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ሙሉ በሙሉ የሻረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን ሲወጡ እንደነበረው ተስፋ ሁሉ ከስድስት ዓመት በፊት የወጣው አዋጅም ለአገሪቱ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል የሚል ግምት ነበር።

❤17
አቶ አዲሱ አረጋ የግብርና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዛሬ ጀምሮ አቶ አዲሱ አረጋን የግብርና ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡
አቶ አዲሱ አረጋ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ገጠር ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ሲያገልግሉ ነበር፡፡
ከዛሬ ጀምሮ የግብርና ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

😁27❤16👍2
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያቀደውን ገቢ ማሳካት እንዳልቻለ ተመላከተ!
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ባለፈው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ለማግኘት ያቀደውን ገቢ ሙሉ በሙሉ ማሳካት አልቻለም። ኮርፖሬሽኑ 146 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ማግኘት የቻለው 124 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ይህም ከታቀደው በ22 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ መሆኑ ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ፣ የውጭ ንግድ ገቢው የእቅዱን 85 በመቶ ያህል ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል። በተቃራኒው፣ በበጀት ዓመቱ የተገኘው አጠቃላይ የ4 ቢሊዮን ብር ገቢ የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም፣ ኮርፖሬሽኑ በተተኪ ምርት እንቅስቃሴ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶች መመረታቸውን ጠቁመዋል፣ ይህም ከእቅዱ በላይ ነው። ከ48,900 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተገልጿል።
Via Capital

❤25👍6🔥2
7 ሳይቶችን በጥራት በታማኝነት አስረክበናል::
ለንግድ ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ
📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት
👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።
ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35
Telegram username
@Ruthtemersales
Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835

❤15
በህገወጥ ግብይት የተሳተፉ 354 የነዳጅ ማደያዎች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው!
በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የተሳተፉ 354 ማደያዎች ላይ ክስ እንዲመሰረትባቸው እየተደረገ ነው አለ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን፡፡የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ የነዳጅ ማደያ ከሌለባቸው አካባቢዎች ውጭ ነዳጅ ከማደያ ውጭ እንዳይሸጥ በህግ ተደንግጓል፡፡
ሆኖም የህግ ድንጋጌውን በመተላለፍ በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የተሳተፉ 354 ማደያዎች ላይ በክልሎች ክስ እየተመሰረተባቸው ነው ብለዋል፡፡በተመሳሳይ ስድስት ኩባንያዎች ለሁለት ወር መታገዳቸውንና ሌሎች ሰባት ኩባንያዎችም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ከዚህም ውስጥ 17 በመቶ የሚሆነው ለኢንዱስትሪዎች፣ ለማዕድን ስራ፣ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ ለመንገድ ግንባታ እንዲሁም ለግብርና ሜካናይዜሽንና ለተለያዩ የልማት ስራዎች ውሏል ነው ያሉት፡፡
(ኤፍ ኤም ሲ)

❤18😁3😭1
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ
በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ዛሬ ማለዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
አደጋው የደረሰው ሲኖትራክ የጭነት ተሸከርካሪ ከሀዋሳ ከተማ ወደ ቱላ ሲጓዝ በነበረበት ወቅት አነስተኛ የከተማ ታክሲ በመግጨት እንዲሁም እግረኞች ላይ በመውጣት የሞትና የአካል ጉዳት ማድረሱ ነው የተገለጸው፡፡
በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ 2 ሰዎች ከባድ ጉዳት አንዲሁም 6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ተብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa

😭10❤5
YeneTube
Photo
ጄ/ ፃድቃን ምን አሉ❓❓👇
" አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት ነባር ወታደራዊ አመራሮች ' ምንቅስቓስ ደለይቲ ለውጢ ' (የለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ) የሚባል ስብስብ ፈጥረናል ! " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ‼️
➡️ " ' ከኮር በላይ በሚሉ የሰራዊት አመራር ነን ' በሚሉ ጥቂት አመራሮችና የሻዕብያ ሰላይ ሰርገ ገቦች ምክንያት ወደ ትግራይ ለመግባት የማልችል መሆኔ እጅግ እጅግ ይቆጨኛል ! "
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ አዲስ የለውጥ እንቅስቃሴ እየመሩ ናቸው።
ጄነራሉ የሚመሩት እንቅስቃሴ " ምንቅስቓስ ደለይቲ ለውጢ (የለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ) ይባላል።
ትላንት ትግራይ ብሮድካስቲንግ ስርቪስ ( TBS) ከተባለ ሚዲያ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉ ሲሆን ሰፊ ጉዳዮችን አንስተዋል።
ምን አሉ ?
➡️ በአቶ ጌታቸው ረዳ እና በራሳቸው በተመራው ጊዜያዊ አስተዳደር ወቅት ፦
- ሁሉም አስተሳሰቦች ማስተናገድ የሚችል ካውንስል እንዲቋቋም ፣
- ለወደፊቱ በምርጫ የሚቋቋሙ የህዝብ ምክር ምክር ቤቶች እውነተኛ የህዝብ ችግር የሚንፀባረቅባቸው እንዲሆኑ ፣
- ብዙህነት አስተሳሰብ የማራመድ ልምድ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥረት ቢያደርጉም እንዳልተሳካ ገልጸዋል።
" ጠቅላይ አስተሳሰብ ካላቸው ቡድኖች ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞኛል " ያሉት ጄነራሉ " በብዙ ጥረት የተለያዩ ፓርቲዎችና አስተሳሰቦች የተካተቱበት ጊዚያዊ ምክር ቤት ቢቋቋምም እንደታለመለት አልቀጠለም " ብለዋል።
የመንግስትንና የፖርቲ መደበላለቅ እንዲለያይ በጥናት የተደገፈ መፍትሄ ቢቀርብም በክልሉ ለ30 ዓመታት በብቸኝነት ተቆጣጠሮ የቆየው የህወሓት አስተሳሰብና አሰራር ሊያራምዳቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል።
በተደረገው ጥናት የ19 ወረዳ አመራሮች በምክር ቤት ሳይሆን በህወሓት የተሾሙ ሆኖው እንደተገኙ ፤ ይህንን ለመቀየር ብዙ ርቀት እንዳይሄዱ ለዓመታት የተተበተበው ኔትወርክ ሊያሰራቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል።
➡️ ጄነራል ፃድቃን ሲመሩት የነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር ተቆጥረው የተሰጡትን ሃላፊነቶች እንዳይወጣ በተለይ የያኔው ምክትል ፕሬዚዳንት የአሁኑ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የሚመራው የፀጥታ ሃይል አኗኗሩ እንዲበላሽ በማድረግ በጊዚያዊ እስተዳደሩ ተቃዉሞ እንዲኖረው በመስራት ለስልጣን መወጣጫ እንደተጠቀመበት ከሰዋል።
➡️ ጄነራሉ " ከኮር በላይ የሰራዊት አመራር ነን " የሚሉ በግላጭ የህወሓት ደጋፊ የሆኑ አካላት ጊዚያዊ አስተዳደሩን አላሰራ አላንቀሳቅስ እንዳሉት ፤ የተከመሩ ችግሮችን ፣ የውጭውን ይቅርና የውስጥ ስራዎችን ለመስራት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
➡️ አሁን ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ስለሚመሩት አስተዳደርም ተናግረዋል። ይህ አስተዳደር ለውጥ የማምጣት አቅምና ቅንነት የለውም ብለዋል።
" ያለፉት 30 ዓመታት በትግራይ የነበረው መንግስትና ፓርቲ አንድ ናቸው የሚል የቆየ አስተሳሰብ ነው እያራመደ ያለው ፤ በዚህ መሰል መንገድ ደግሞ በአሁናዊ የትግራይ ሁኔታ ህዝብን የሚጠቅም ለውጥ ማምጣት አይቻልም " ብለዋል።
" አሁን ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ወደ ስልጣን የመጣበት መንገድ ትክክለኛ አይደለም " ያሉት ጄነራሉ " የህዝብ አጀንዳ ያለው አስተዳደር አይደለም ፣ ለዚህ ነው በደቡባዊና ደቡባዊ ምስራቅ ዞን የሚታየው የህዝብ ንቅናቄ ለማፈን የሚንቀሳቀሰው " ብለዋል።
➡️ ጄነራሉ ቢያንስ 49 (ተፎኳኳሪዎች) በ51 (ህወሓት) የነበረው የጊዚያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር አሁን መቶ በመቶ በሚባል መልኩ በህወሓት ቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን አሳውቀዋል።
" የፌደራል መንግስት ለዚህ መሰል አስተዳደር ትግራይ እንዲመራ ፍቃደኝነት ማሳየቱ በበኩሌ የምቀበለውና የሚገባኝ አይደለም " ብለዋል።
➡️ አዲሱን የለውጥ ስብስብ በተመለከተም ጄነራል ፃድቃን " የትግራይ ህዝብ መሪ ነው ያጣው እንጂ ለለውጥ ዝግጁ ነው ፤ በመሬት ላይ የምናየው ይህንን ነው ይህንን የለውጥ ፍላጎት በሰላማዊ መንገድ በተገቢው መመራት አለበት " ብለዋል።
" ከዚህ በመነሳት አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት ነባር ወታደራዊ አመራሮች ' ምንቅስቓስ ደለይቲ ለውጢ ' (የለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ) የሚባል ስብስብ ፈጥረናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ይህ የተፈጠረው ፦
- በዓረና ፣
- በውናት፣
- በባይቶና ፣
- በስምረት ሲሆን ፣ ወታደራዊ አመራሮቹ ደግሞ እኔ (ጀነራል ፃድቃና) እና ጀነራል ተኽላይ አሸብር ነን " ሲሉ ተናግረዋል።
" የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ እኔ ነኝ " ያሉት ጄነራሉ " የፈጠርነው እንቅስቃሴ ምንጭ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሆኖ ጦርነት መልሶ እንዳይጀመር ለመከላከል ፣ የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ ለመስራት ሲሆን ፣ ዋነኛ ዓላማዎቹ ሦስት ሆነው እነሱ ደግሞ ፦
- መንግስት ስለ ሌለ መንግስት መመስረት ፣
- በትግራይ ጦርነት እንዳይፈጠር ድምፅ መሆን ፣
- ህወሓት ቅቡልነት ስለአጣ ለመተካትና ለቀጣይ ምርጫ ለመዘጋጀት የሚሉ ናቸው " ብለዋል።
" የጀመርነው ለውጥ የእኛ ሳይሆን የተተኪው ሃይል ድርሻ ነው ፣ እኛ እያደርግን ያለነው ለተተኪው መንገዱን የማሳየት ስራ ነው፣ የትግራይ ህዝብ በተለይ ወጣቱ የጀመርነው እንቅስቃሴ ባለቤት መሆኑ ማወቅና መደገፍ አለበት ፣ የፌደራል መንግስትም ይህንን የለውጥ ጥያቄ የመደገፍ ሃላፊነት አለበት " ሲሉ ገልጸዋል።
➡️ ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ " ህዝቡ ምርጫዬ ሰላም ነው እምቢ ለጦርነት ማለት መቻል አለበት ፣ የአንድ ፓርቲ የእድሜ ልክ አገዛዝ በቃኝ የብዙሃን አመራር ነው የምፈልገው ማለት መቻል አለበት " ብለዋክ።
" ' ከኮር በላይ በሚሉ የሰራዊት አመራር ነን ' በሚሉ ጥቂት አመራሮችና የሻዕብያ ሰላይ ሰርገ ገቦች ምክንያት ወደ ትግራይ ለመግባት የማልችል መሆኔ እጅግ እጅግ ይቆጨኛል " ያሉት ጄነራሉ " ወደ ትግራይ መግባት የሚከለክል ይህንን መሰል አደገኛ ፖለቲካ ቶሎ መቀየር አለበት " ብለዋል።
" እንደ ህዝብ የሚያጠፋን ፖለቲካ ቶሎ እንዲቀየርና ምዕራፉ እንዲዘጋ ተቀናጅተን በጋራ መታገል አለብን " ሲሉ አክለዋል።
" ' የትግራይ የሰላም ሃይል ' በሚል የተጀመረውን የሰራዊት እንቅስቃሴ እደግፈወለሁ " ያሉት ጄነራሉ የትግራይ ኃይል አባላት እንዲቀላቀሉት ፤ ወጣቶች በራያ በዓዲጉዶምና ሌሎች አከባቢዎች የጀመሩትን የእምቢታ እንቅስቃሴ እንቂቀጥሉም ጥሪ ሲያቀርቡ ተደምጠዋል።
ቃለ ምልልሱ የተወሰደው ከTBS ቴሌቪዥን ነው።

❤60
በትግራይ ክልል ቆላ ተንቤን በተከሰተ ድርቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶች ሞቱ!
በማዕከላዊ ትግራይ ቆላ ተንቤን ወረዳ በዚህ ሳምንት በተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተገለፀ።በድርቁ በያከር አካባቢ ብቻ ከ18,000 በላይ የቤት እንስሳት ሲሞቱ፤ በመቶዎች የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬት ደግሞ ወድሟል።
ይህም አሁን ላይ ከጦርነት ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባላገገመው ክልሉ ውስጥ ረሀብ ሊመለስ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ጎይቶም ገብረሐዋሪያ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ዝናብ ባለመኖሩ እና በመኖ እጥረት ምክንያት 184 ከብቶች፣ 900 አህዮች፣ ከ4,500 በላይ በጎች፣ ከ13,000 በላይ ፍየሎች ሞተዋል። አያይዘውም "እስከዛሬ ድረስ ዝናብ በአካባቢው አልጣለም"ሲሉ ገልጸው "ንቦችም ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል" ሲሉ አክለዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ በህፃናትና በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ምልክቶች፣ እንደ እብጠት ያሉ እና ሌሎችም ከረሃብ ጋር የተያያዙ ምልክቶች እየታዩ ነው።በድርቁ ምክንያት 650 ሄክታር የእርሻ መሬት ሳይዘራ የቀረ ሲሆን 50 ሄክታር ሰሊጥ ደግሞ መብቀል አለመቻሉን ጠቁመዋል።

😭33❤18
በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚንየም ዉስጥ ብሎክ 415 የምትኖር አንዲት ሴት በሰራተኛው ላይ ባደረሰችዉ ጉዳት በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ዉላለች።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
😭56❤16
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መቀመጫቸውን አሜሪካ በማድረግ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝነት ለመናድ እየሰሩ ናቸው ያላቸውን የገንዘብ አስተላላፊዎችን ይፋ አደረገ ⵑⵑ
ባንኩ ዛሬ ለውጭ አገር ለሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሚል ባወጣው መግለጫ
ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን እና አሸባሪዎችን የገንዘብ ድጋፍን ለመከላከል ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ዝውውሮች በመደበኛ እና በተስተካከለ የፋይናንስ ስርዓት መከናወን አለባቸው።
ከዚህ መርህ በተቃራኒ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝነት ለመናድና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በግልጽ በማሰብ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ በርካታ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በውጭ አገር ከሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ የተሰበሰቡ ገንዘቦችን በመጠቀም በገንዘብ ማሸሽ ተግባር ላይ የተሰማሩና ሕገ-ወጥ ተግባራትን በገንዘብ የሚደግፉ መሆናቸውን ተለይተዋል ።
ባንኩ መቀመጫቸውን አሜሪካ በማድረግ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ታማኝነት ለመናድ እየሰሩ ናቸው ያላቸውን የገንዘብ አስተላላፊዎችን ዝርዝር በመግለጫው አካቷል በዚህም መሰረት
1. Shgey Money Transfer - Silver Spring, MD, and Falls Church, VA, USA
2. Adulis Money Transfer - Falls Church, VA, and Silver Spring, MD, USA
3. Ramada Pay (Kaah) - Falls Church, VA, USA
4. TAAJ Money Transfer - Minneapolis, MN, USA
በተዘረዘሩት ተቋማት ላይ የሚመለከታቸው አካላት ምርመራ በማካሄድ እንዲተባበሩ ባንኩ ጠይቋል፡፡
[KGEthiopia]

❤33😁15👍6🔥1
በሰው መነገድ ወንጀል ላይ የተሳተፉ 5 ሰዎች ሞት ተፈረደባቸው!
በሰው መነገድ ወንጀል ላይ በተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወሰን መደረጉን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የብዙ የሰዎች ህይወት እየቀጠፈ ያለ ወንጀል ነው፡፡
በወንጀሉ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወንጀለኞች በአዋጅ ቁጥር አንድ ሺህ 178 መሰረት የሞት ቅጣት፣ የዕድሜ ልክ እስራትና እስከ 25 ዓመት እስራት ያስቀጣል ብለዋል፡፡በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሂደቱ የተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወስን መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በሰው የመነገድ ወንጀል ለመከከላከልና ለመቆጣጠርም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና በክልሎች መካከል ቅንጅትና ትብብር የሚፈጥሩ ስራዎችና መመሪያ የማጽደቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡በተጨማሪም በህገወጥ ድርጊቱ በስፋት ተጠቂ ለሆኑት ወጣቶች በሀገር ወስጥ የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልም ድንበር ተሻጋሪ የተደራጀ ወንጀል መሆኑን አንስተው፤ ይህንንም ለመቆጣጠር ከጅቡቲ፣ ኬንያና ማላዊ ጋር ዓለም አቀፍ ትብበር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በመሆኑም ባለፈው በጀት ዓመት የተወሰደው የህግ እርምጃ እንደሀገር የተሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው፡፡በቀጣይም የተሻለ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Via Gazette Plus

❤38👍6⚡1